newsare.net
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በረኅብ ለተጎዱ ሰዎች የርዳታ እህል ወደ ወረዳው እንዲገባ ከመንግሥትና ከፋየእህል ርዳታ ወደ ቡግና ወረዳ መጓጓዝ መጀመሩን ባለሥልጣናት አስታወቁ
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በረኅብ ለተጎዱ ሰዎች የርዳታ እህል ወደ ወረዳው እንዲገባ ከመንግሥትና ከፋኖ ታጣቂዎች ጋራ ስምምነት ማድረጋቸውን አስታወቁ። በስምምነቱ መሰረትም የርዳታ እህሉ እየገባ መኾኑን አንድ የኃይማኖት አባት ተናግረዋል። የሰሜን ወሎ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል፣ አካባቢው በፋኖ ታጣቂዎች ስር በመኾኑ ለተከሰተው የምግብ እጥረት መንግሥት በቶሎ ምላሽ መስጠት አልቻለም ብለዋል። የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በአደረጉት ጥረትም ከ110 ሺሕ በላይ ለሆኑ ሰዎች ከ16 ሺሕ ኩንታል በላይ የርዳታ እህል ወደ ስፍራው እየተጓጓዘ መኾኑን አስታውቀዋል። የወረዳው ነዋሪ ያለበትን የምግብና የጤና ችግር ለፋኖ ታጣቂዎችና ለመንግሥት አካላት ለማስረዳት ከተመረጡት 18 ግለሰቦች መካከል “አንዱ ነበርኩ” ያሉት ቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዝናቤ ይርዳው በአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረሰው ስምምነት መድኃኒቶችንና አልሚ ምግቦች ወደ ወረዳው መግባት መቻላቸውን ተናግረዋል። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ሁለት የአይና ቡግና ወረዳ ነዋሪ እናቶች፣ ለሕፃን ልጆቻቸው አልሚ ምግቦችን ከጤና ተቋማት ተቀብለው ወደ ቤታቸው እየሄዱ እንደሆነ ተናግረዋል። በሌላ በኩል አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ዛሬ ታኅሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በፌስ ቡክ ገጹ በአወጣው መግለጫ በቡግና ወረዳ የምግብ እጥረት ቀውስ ሰለመኖሩ የወጡ ሪፖርቶችን እየተከታተለ መኾኑን አመልክቷል። «ሁኔታውን መከታተላችንን እና መገምገማችንን እንቀጥላለን» ያለው መግለጫው ቀውሱ መወገዱን ለማረጋገጥ እንደሚሠራም ጠቅሷል። ኤምባሲው በመግለጫው ቀውሱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን አላካተተም። የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመደገፍ ፣ አጋሮቹ በአኹኑ ሰዓት በችግሩ በተጠቁት አብዛኞቹ ስፍራዎች የምግብ እና አልሚ ንጥረ ምግቦች ስርጭትን ያጠናከሩ መሆናቸውንም አክሏል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more