newsare.net
ደቡብ ኮሪያ ውስጥ ፣ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን የማኮብኮቢያ ረድፉን ጥሶ ከኮንክሪት አጥር ጋር በመጋጨቱ በትንሹ 179 ሰዎች በእሳት ጋይተው መሞታቸውን ባለበደቡብ ኮሪያ በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ 179 ሰዎች ሞቱ
ደቡብ ኮሪያ ውስጥ ፣ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን የማኮብኮቢያ ረድፉን ጥሶ ከኮንክሪት አጥር ጋር በመጋጨቱ በትንሹ 179 ሰዎች በእሳት ጋይተው መሞታቸውን ባለስልጣናት ተናገሩ። የጄጁ ኤር ንብረት የሆነው መንገደኛ ጫኝ አውሮፕላን ሙዐን በተባለችው ፣ ከመናገሻዋ ከተማ ሲዮል በስተደቡብ በምትገኝ ከተማ ለማረፍ በሚሞክርበት ቅጽበት ነው አደጋው የተከሰተው። 181 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረው አውሮፕላን ከታይላንድ ባንኮክ እየተመለሰ ነበር።አደጋው በሀገሪቱ የበረራ ታሪክ እጅግ አስከፊ ከሆኑት አንዱ እንደሆነ ተነግሯል ። የድንገተኛ አደጋ መከላከል ሰራተኞች ሁለት የአውሮፕላኑን ሰራተኞች ማዳናቸውም ተሰምቷል ። ሁለቱም ሰዎች ለህይወት አስጊ አደጋ እንዳልገጠማቸው ባለስልጣናት ተናግረዋል። ተሳፋሪዎቹ በብዛት ደቡብ ኮሪያውያን ሲሆኑ ፣ ሁለቱ የታይላንድ ዜጎች ነበሩ። የትራንስፖርት ሚኒስቴር ባለስልጣናት ቀደም ብለው ባደረጉት የግንኙነት መሳሪያዎች ግምገማ ፣ የአውሮፕላን ማረፊያው መቆጣጠሪያ ማማ ሰራተኞች ፣ አውሮፕላኑ ለማረፍ ከማቀዱ ጥቂት ቀደም ብሎ አዕዋፍት ከአውሮፕላኑ ጋር ሊጋጩ ይችላሉ የሚል የስጋት ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን እና አብራሪው ሌላ ቦታ እንዲያርፍ መፍቀዳቸውን ያሳያል። የታይላንድ አየር ማረፊያዎች ኃላፊ ኬራቲ ኪጅማናዋት በሰጡት መግለጫ የጄጁ ፣ በረራ 7C 2216 አውሮፕላን ፣ ከሱቫርናብሁሚ አየር ማረፊያ ሲነሳ ፣ ምንም የተለየ ሁኔታ እንዳልተመዘገበበት አረጋግጠዋል። ጄጁ ኤር በሰጠው መግለጫ ለአደጋው ጥልቅ ይቅርታ ከጠየቀ በኃላ ፣ የድህረ አደጋ ሁኔታዎችን ለመቆጣጠር የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ አስታውቋል። በቴሌቭዥን በተላለፈው የጋዜጠኞች ማስገንዘቢያ ላይ የጄጁ ኤር ፕሬዝዳንት ኪም ኢ-ባ ከሌሎች የኩባንያው ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን በይቅርታ ደንብ እጅ በመንሳት የሟቾችን ቤተሰቦች ይቅርታ ጠይቀው ፣ ለክስተቱ “ሙሉ ሀላፊነት” እንደሚሰማቸው ተናግረዋል። ኪም አየር መንገዱ በወቅቱ ባደረገው ምርመራ በአውሮፕላኑ ላይ ምንም ዓይነት የሜካኒካል ችግር አለመኖሩን እና የአደጋውን መንስኤ በተመለከተ የመንግስት የምርመራ ውጤቶችን እንደሚጠባበቅ ተናግረዋል። (ዘገባው የአሶሼትድ ፕረስ ነው) Read more