newsare.net
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር በ100 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ካርተር ከፕሬዚደንትነታቸው በፊት በለውዝ ግብርና ስራ እንዲሁም በየቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር በ100 ዓመታቸው አረፉ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር በ100 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ካርተር ከፕሬዚደንትነታቸው በፊት በለውዝ ግብርና ስራ እንዲሁም በጆርጂያ ግዛት አስተዳዳሪነት ሀገራቸውን አገልግለዋል። ካርተር በአውሮፓዊያኑ አቆጣጣር ፣ ጥር 20 ቀን 1977 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ሆነው ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ «እንደ ሀገሪቱ ህዝብ ሁሉ መልካም መንግስት» እንደሚመሰርቱ ቃል ገብተው ነበር። አራት ዓመት የስልጣን ዘመናቸው ግን ርጋታ የራቀው ነበር።ያሻቀበ የዋጋ ንረት እና የስራ አጥነት ቁጥር መጨመር አስተዳደራቸው ቅድሚያ ሊሰጣቸው ያቀዳቸውን ጉዳዮች አስተጓጉሏል። በግብፅ እና በእስራኤል መካከል የሰላም ስምምነት እንዲደረስ በማድረግ እና የፓናማ ካናል ስምምነትን እውን በማድረግ በውጭ ፖሊሲ መስክ ድሎችን አስመዝግበዋል። ኢራን ውስጥ የነበረው የአጋች ታጋች ቀውስ መዘዝ በኋይት ሀውስ የነበራቸውን ቆይታ የመጨረሻዎቹን ዓመታት ተቆጣጥሮ በ1980ው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ እንዲሸነፉ አድርጓቸዋል። ጂሚ ካርተር ዋይት ኃውስን መናገሻ ካደረጉ የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች ሁሉ ዕድሜ ጠገቡ የነበሩ ሲሆን ፣ ከባለቤታቸው ሮሳሊን ጋር ያሳለፉት 76 ዓመት የትዳር ዘመንም ከትኛውም አሜሪካ ፕሬዚደንት ትዳር ዘመን ጋር ሲነጻጸር ረጅሙ ሆኖ ተመዝግቧል ። Read more