newsare.net
ኢትዮጵያ ዛሬ አርብ የአክሲዮን ገበያ መጀምሯን ይፋ አደረገች። ርምጃው እየተከመ የመጣውን ኢኮኖሚዋን ነፃ ለማድረግ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህኢትዮጵያ የአክሲዮን ገበያ ጀመረች
ኢትዮጵያ ዛሬ አርብ የአክሲዮን ገበያ መጀምሯን ይፋ አደረገች። ርምጃው እየተከመ የመጣውን ኢኮኖሚዋን ነፃ ለማድረግ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከያዙት ጥረት የቅርብ ጊዜው ተደርጎ ተወስዷል። በአክሲዮን ገበያው የተመዘገበው የመጀመሪያ ኩባንያ መንግሥታዊው ኢትዮ ቴሌኮም ሲኾን፤ የተለያዩ ባንኮችን እና የመድን ኢንሹራንስ ኩባንያዎችን ጨምሮ በደርዘን የሚቆጠሩ ሌሎች የንግድ ተቋማትም በቅርቡ ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል። በ2010 ዓ.ም ሀገሪቱን የመምራት ሥልጣን ከያዙ በኋላ፣ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያለውን ኢኮኖሚ ለነጻ ገበያ እና ለውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ክፍት ለማድረግ ያላቸውን ፍላጎት ያመለከቱት አብይ፣ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2020 እስከ 2022 ባለው ጊዜ በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደውን አስከፊ የእርስ በርስ ጦርነት ጨምሮ በሃገሪቱ እየተካሄዱ ያሉ ግጭቶችን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችው ማዕቀብ፡ የኢኮኖሚ ተሃድሶው እንደተባለው መሄድ ያለመቻሉ ተዘግቧል። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ቅርብ ወራት ውጥስ የውጭ መዋዕለ ንዋይ ለመሳብ በሚል በርካታ የኢኮኖሚ ተሃድሶ ርምጃዎችን መውሰዱ ይታወቃል። በቅርቡም የኢትዮጵያ ፓርላማ የውጭ ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፎችን እንዲከፍቱ የሚፈቅድ ሕግ አጽድቋል። ሆኖም ሕጉ የዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ይዞታ እስከ 49 በመቶ የሚኾነውን አክሲዮን ድርሻ ብቻ እንዲይዙ እገዳ ይጥላል። በሌላ ተዛማች ዜና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው የጥቅምት ወር ያዘጋጀው የመጀመሪያው የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ሽያጭ እስከ 10 በመቶ የሚሆነውን የአክሲዮን መሸጥ መፍቀዱን ይፋ አድርጓል። ኢትዮጵያ የሃገሪቱ መገበያያ የሆነው ብር ዶላር የመግዣ ዋጋ በነፃ ገበያ እንዲወሰን የሚያስችል ከፍተኛ የምንዛሪ ዋጋ ማሻሻያ ለውጥ ባለፈው ሐምሌ ወር ይፋ ማድረጓም አይዘነጋም። ይሁንና የኢትዮጵያ ብር የዶላር አቅም ይበልጥ መዳከም እየታየበት መጥቷል። ኢትዮጵያ ከ1967 የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት መውደቅ እና ማርክሳዊ ሥርዐት ያራምድ የነበረው ደርግ ኢኮኖሚውን በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ካዋለበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት 50 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የአክስዮን ገበያ አልነበራትም። Read more