newsare.net
በሰሜናዊ ምስራቅ ናይጄሪያ፣ ቦርኖ ግዛት ውስጥ እስላማዊ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት፣ ቢያንስ 40 ገበሬዎች መግደላቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ዛሬ ሰኞ አስታበሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ እስላማዊ ታጣቂዎች ቢያንስ 40 ገበሬዎችን መግደላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ
በሰሜናዊ ምስራቅ ናይጄሪያ፣ ቦርኖ ግዛት ውስጥ እስላማዊ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት፣ ቢያንስ 40 ገበሬዎች መግደላቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ዛሬ ሰኞ አስታወቁ። ጥቃቱ የተፈፀመው እሑድ ዕለት ሲሆን፣ ለጥቃቱ የቦኮ ሃራም ቡድን እና ከቡድኑ ተገንጥሎ የወጣ እና በቦርኖ ግዛት የሚንቀሳቀስ ለእስላማዊ መንግሥት ታማኝ መኾኑ የተገለፀ ቡድን ተጠያቂ መደረጋቸውን የቦርኖ ግዛት አስተዳዳሪ የሆኑት ባባጋና ኡማርራ ዙሉም ተናግረዋል። አስተዳዳሪው አክለው፣ ሲቪሎች «ደኅንነታቸው የተጠበቁ ዞኖች» ተብለው ከጠቀሷቸው እና የጦር አባላት ከፅንፈኞች እና ከተቀበሩ ፈንጂዎች እንዳፀዷቸው ከገልጿቸው አካባቢዎች እንዳያልፉ አስጠንቅቀዋል። አክለውም ታጣቂዎቹ ያደረሱት ጥቃት ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ጠይቀዋል። በናይጄሪያ የተመሰረተው ቦኮ ሃራም፣ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ምዕራባዊ የትምህርት አሰጣጥን ለመዋጋት እና አክራሪ እስላማዊ ሕግን ለመጫን የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ ቆይቷል። አፍሪካ ከታጣቂዎች ጋራ ካደረገቻቸው ትግሎች ረጅሙን ጊዜ መፍጀቱ የተገለጸው ግጭትም፣ ከናይጄሪያ አልፎ በስተሰሜን የሚገኙ የጎረቤት ሀገራትም ተስፋፍቷል። ታጣቂዎቹ እስካሁን ባደረሷቸው ጥቃቶች ቢያንስ 35 ሺሕ ንፁሃን ዜጎች የተገደሉ ሲኾን፣ በሰሜን ምስራቃዊ የናይጄሪያ አካባቢ የሚኖሩ ከ2 ሚሊየን በላይ ሰዎች ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል። Read more