newsare.net
በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ግዛት ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰው ያለውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሠራተኞች ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ባሉበት ወቅት፣ እንደአዲየካሊፎርኒያ ሰደድ እሳት ከቁጥጥር ውጪ ኾኖ ሊባባስ ይችላል ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ትንበያዎች አስጠነቀቁ
በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ግዛት ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰው ያለውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሠራተኞች ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ባሉበት ወቅት፣ እንደአዲስ ሊባባስ ይችላል ተብሎ የተሰጋው ጠንካራ ንፋስ እሳቱን ሊያባብሰው እና ከቁጥጥር ውጪ ሊያደርገው ይችላል ሲሉ የትንበያ ባለሞያዎች አስጠንቅቀዋል። የአሜሪካ ብሔራዊ የአየር ትንበያ አገልግሎት በአወጣው ማስጠንቀቂያ፣ ነገ ማክሰኞ ሊጨምር ይችላል ተብሎ የተሰጋው ጠንካራ ንፋስ በሰዓት ከ80 እስከ 110 ኪሎሜትር ሊጓዝ ይችላል ብሏል። ከስምንት ወራት በላይ በቂ ዝናብ ሳይገኝ በቆየው አካባቢ የሚገኘው ደረቅ የአየር ሁኔታ እና ጠንካራ ንፋስ፣ ሰደድ እሳቱ እንዲባባስ ምክንያት ኾኗል። ለአንድ ሳምንት በዘለቀው እሳት እስካሁን የ24 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲኾን፣ በቢሊየኖች የሚቆጠር ንብረትም አውድሟል። ከሟቾቹ መካከል ስምንቱ በፓሲፊክ ፓሊሳዴስ አካባቢ በተዛመተው እሳት የሞቱ መሆናቸውን ባለስልጣናት ያስታወቁ ሲሆን ከ12 ሺህ በላይ ቤቶች እና ህንፃዎች ወድመዋል። እስከ ትላንት እሁድ ምሽት ድረስ 100 ሺህ ሰዎች ከአካባቢያቸው ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው ሲሆን፣ አዲስ ንፋስ ሊነሳ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ መውጣቱን ተከትሎ ነዋሪዎቹ ወደ መኖሪያቸው መመለስ እንደማችሉ ተመልክቷል። እሳቱ እየተስፋፋ መሄድ መቀጠሉን ተከትሎም፣ የአካባቢው ባለስልጣናት፣ ሕዝብ በብዛት የሚኖርባቸውን አካባቢዎች እና እንደ ፖውል ጌቲ ሙዚየም እና ታዋቂ ከሆኑ የአሜሪካ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንዱ የሆነው የካሊፎርኒያ ዩንቨርስቲን የመሳሰሉ፣ የከተማዋን ቁልፍ ምልክቶች ሊያወድም ይችላል የሚል ስጋታቸውን እየገለፁ ነው። እስካሁን በተደረጉ ቅድመ ጥናቶች መሠረት፣ እሳቱ በንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት እና የኢኮኖሚ ኪሳራ ከ130 እስከ 150 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። የካሊፎርኒያ ግዛት አስተዳዳሪ ጋቪን ኒውሶም ከኤን ቢ ሲ የቴሌቭዥን ጣቢያ ጋራ ባደረጉት ቃለምልልስ እሳቱ እንዴት ሊነሳ እንደቻለ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቀዋል። Read more