newsare.net
የእስራኤል ሚኒስትሮች ካቢኔ በጋዛ ተኩስ እንዲቆም እና ታጋቾቹ እንዲለቀቁ የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት አጽድቋል። ስምምነቱን ሀያ አራት ሚንስትሮየእስራኤል ካቢኔ የተኩስ አቁም ስምምነቱን አጸደቀ
የእስራኤል ሚኒስትሮች ካቢኔ በጋዛ ተኩስ እንዲቆም እና ታጋቾቹ እንዲለቀቁ የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት አጽድቋል። ስምምነቱን ሀያ አራት ሚንስትሮች ሲደግፉ ስምንት ሚንስትሮች ውድቅ አድርገውታል። ተኩስ አቁሙ ሰኞ ከሚከናወነው በዩናይትድ ስቴትስ የተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በዓለ ሲመት ዋዜማ እሑድ ጀምሮ ሥራ ላይ ሊውል ታቅዷል። እስራኤል እና ሀማስ ተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የደረሱት በዩናይትድ ስቴትስ በካታር እና በግብጽ ሽምግልና ከአንድ ዓመት በላይ የፈጀ ድርድር ከተካሄደ በኋላ ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በግንቦት ወር ያጸደቁትን የተኩስ አቁም ስምምነት ሁለቱ ወገኖች በዚህ ሳምንት ረቡዕ ፈርመዋል። በማስከተልም የእስራኤል ካቢኔ ይሁንታ ሰጥቶታል። ሰኞ ቃለ መሐላቸውን ፈጽመው አስተዳደሩን የሚረከቡት ዶናልድ ትረምፕ የስምምነቱን ተግባራዊነት መከታተሉ የእርሳቸው አስተዳደር ኃላፊነት ይሆናል። Read more