newsare.net
በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ውል ዛሬ እሁድ ሥራ ላይ ውሏል። ስምምነቱ ጋዛ ላይ ለዐስራ አምስት ወራት የቀጠለውን ጦርነት ለስድስትተኩስ አቁሙ ተግባራዊ ኾነ፣ ሃማስ የመጀመሪያዎቹን ታጋቾች ለቀቀ
በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ውል ዛሬ እሁድ ሥራ ላይ ውሏል። ስምምነቱ ጋዛ ላይ ለዐስራ አምስት ወራት የቀጠለውን ጦርነት ለስድስት ሳምንታት በሚገታው የተኩስ አቁም ውል መሠረት የሃማስ ታጣቂዎች የያዟቸውን በርካታ ታጋቾች እንዲለቅቁ ይጠይቃል። ዛሬ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ በሰዓታት ውስጥ ሃማስ የመጀመሪያዎቹን ሦስት ወጣት ሴቶች የለቀቀ ሲሆን ቀይ መስቀል በአጀብ ወደ ጋዛ በመግባት የተለቀቁትን ታጋቾች ተረክቧል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሃማስ ዛሬ እሁድ ይለቃል የተባለውን ሦስት ታጋቾች ስም ዝርዝር ሳይሰጠን ስምምነቱ ተግባራዊ አይሆንም በማለታቸው ተግባራዊ የሆነው ከታቀደው ሰዓት በሦስት ሰዓት ገደማ ዘግይቶ ነው። ኔታንያሁ በአገሩ ሰዓት ጠዋት ሁለት ተኩል ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የታቀደው ተኩስ አቁም ሃማስ «እሰጣለሁ» ያለውን የሚለቀቁ ታጋቾች ስም ዝርዝር ሳይሰጥ ተግባራዊ እንዳይሆን ለመከላከያ ኃይሎች ትዕዛዝ ሰጥተዋል ሲል ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ አስታውቋል። ይህንኑ ተከትሎ ሃማስ ስም ዝርዝሩን ከሰጠ በኋላ እስራኤል ተኩስ አቁሙ አምስት ሰዓት ተኩል ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን አስታውቃለች። ሃማስ ስም ዝርዝሩ የዘገየው በቴክኒክ እክል ምክንያት እንደሆነ ጠቅሶ ስምምነቱን እንደማከብር በድጋሚ አረጋግጣለሁ ሲል መግለጫ አውጥቷል። ይህ በዚህ እንዳለ አክራሪ ብሔርተኛው የእስራኤል የብሔራዊ ጸጥታ ሚንስትር ኢታማር ቤን ጋቪር የተኩስ አቁም ውሉን በመቃወም ሥራ መልቀቃቸው ተዘግቧል። Read more