newsare.net
ዛሬ ሰኞ በድጋሚ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንትነትን የተረከቡት ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትረምፕ «ምክንያት ላይ የተመሠረተ የአስተሳሰብ አብዮት» ጥሪ በማቅዶናልድ ትራምፕ የፕሬዝደንትነት ሥልጣናቸውን ተረከቡ
ዛሬ ሰኞ በድጋሚ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንትነትን የተረከቡት ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትረምፕ «ምክንያት ላይ የተመሠረተ የአስተሳሰብ አብዮት» ጥሪ በማቅረብ፣ በሚፈልጉት መንገድ የአሜሪካን የፖለቲካ ምሕዳር ለመለወጥ በርካታ አስፈፃሚ ትዕዛዞችን መፈረም እንደሚጀምሩ ተናግረዋል፡፡ ትረምፕ ቃለ መሐላቸውን በምክር ቤቱ ህንፃ ውስጥ በፈጸሙበት ወቅት በአሰሙት ንግግራቸው “የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን” መጀመሩን እና ለፈጣን የፖሊሲ ለውጦች የአስፈፃሚ ትእዛዝ መሰጠቱን”ተናግረዋል። ትረምፕ ዋሽንግተን ውስጥ እጅግ ቀዝቃዛ በኾነው ቀን፣ የጀመሩት ከባለቤታቸው ሜላኒያ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋራ ሲኾን ስነ ስርዐቱን የጀመሩት በወጉ መሰረት ለአዲስ ፕሬዝዳንቶች በሚደረገው ከዋይት ሐውስ ፊት ለፊት ካለው የመናፈሻ ስፍራአቅራቢያ በሚገኘው በቅዱስ ዮሀንስ ኤጲስ ቆጶስ ቤተክርስቲያን በተደረገው ጸሎት ነው፡፡ ትራምፕ ከተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ከቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን ጋራ ከበዓለ ሲመቱ አስቀድሞ በኋይት ሃውስ ለሻይ ሥነ ሥርዐት ተገናኝተው ነበር፡፡ 45ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶናልድ ትረምፕ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ካፒቶል ውስጥ ነው ወደ 600 ሰዎች በተገኙበት ሥነ ሥርዐት፣ ለሁለተኛ ጊዜ 47ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት በመኾን ቃለ ቃለ መሐማ ፈጽመዋል። “እኔ ዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በሚያዘው መሰረት፣ ሕግ መንግሥቱን ለማስጠበቅ፣ ለመመከት እና ለመከላከል አቅሜ በፈቀደው ሁሉ ኃላፊነቴን በታማኝነት ለመወጣት ቃል እገባለሁ። ለዚህም ፈጣሪ ይርዳኝ!” ብለዋል። በ1890ዎቹ ከግሮቨር ክሊቭላንድ በኋላ ፕሬዝዳንት ተከታታይ ባልኾኑ የሥልጣን ዘመናት በማገልገል ትረምፕ ሁለተኛው ይሆናሉ፡፡ በ78 ዓመታቸው ፕሬዝዳንት በመሆን ትረምፕ በዕድሜ ትልቁ ሲሆኑ፣ ባይደን ከአራት ዓመት በፊት ቃለ መሐላ ሲፈጽሙ ከሳቸው በአምስት ወር ያንሱ ነበር፡፡ የ40 ዓመቱ ቫንስ፣ 50ኛው ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን በታሪክ ሦስተኛው በእድሜ ትንሹ ያደርጋቸዋል ፡፡ ትረምፕ ባለፈው ዓመት ለወሲብ ፊልም ተዋናይ ስቶርሚ ዳንኤልን የተከፈለውን የ130 ሺሕ ዶላር የአፍ ማስያዣ ገንዘብ ለመደበቅ የቢዝነስ ሰነድ አጭበርብረዋል በሚል ተከሰዋል፡፡ በዚሁ ክስ በ34 የወንጀል ክሶች ጥፋተኛ ተብለው ተፈረደባቸዋል፥፥ በኋላ ምንም ዳኛው ቅጣት ውሳኔ እንደማይሰጡ ቢያስታውቁም፣ በወንጀል ክስ በጥፋተኝነት የተፈረደባቸው የመጀመሪያው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ይሆናሉ። ሪፐብሊካኑ ትረምፕ ባይደን እንደ አውሮፓያን አቆጣጠር በ2020 ያሸነፉበትን የምርጫ ውጤት በሕገ ወጥ መንገድ ለመቀልበስ ሞክረዋል የሚለው ክስ ተቋርጧል፡፡ ክሱ የተቋረጠው ትረምፕ የዲሞክራቲክ ፓርቲው ተቀናቃኛቸውን ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስን በምርጫ አሸንፈው በመመረጣቸው ሥልጣን ላይ ያሉ ፕሬዚዳንቶች አይከሰሱም በሚለው በፍትህ ሚኒስቴር ፖሊሲ ምክንያት ነው። ፕሬዝደንታዊ በዓለ ሲመቱ ወደ 250 ዓመት የሚጠጋው የአሜሪካ ዲሞክራሲ መለያ የሆነው በየአራት ዓመታት የሚመጣው ሰላማዊ የፕሬዚዳንት ስልጣን ሽግግር ሲሆን፣ ለወትሮው የሚከናወነው250 ሺሕ ሰዎችን ወይም ከዚያ በላይ በሚይዘው በተንጣለለው ናሽናል ሞል መስክ ትይዩ በሚገኘው የምክር ቤቱ ህንፃ ደጃፍ ላይ ነው፡፡ በቃለ መሐላው ስነ ሥርዐት ዋዜማ እሁድ ሌሊቱን ወደ ዋሽንግተን የነፈሰው ቀዝቃዛ አየር፣ እጅግ ከባድ ብርድ ማስከተሉ በፈጠረው ስጋት የተነሳ ሥነ ሥርዐቱ ምክር ቤት ህንጻ «ካፒቶል ሮተንዳ» አዳራሽ እንዲከናወን ተውስኗል፥ ስነ ስርዐቱ በትረምፕ ትዕዛዝ ወደ ምክር ቤቱ ህንጻ ውስጥ እንዲዛወር በመደረጉ፣ በአካል ተገኝተው የሚመለከቱት ወደ 600 የሚጠጉ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ካፒቶል 2 ሺሕ የሚደርሱ የትረምፕ ደጋፊዎች እ.ኤ.አ. በ2021ዓ.ም የምክር ቤቱን ህንፃ በመውረር በባይደን የተሸነፉበትን የምርጫ ውጤት እንዳያጸድቅ ለማድረግ የሞከሩበት ስፍራ ነው፡፡ በአርባ ሰባተኛው ፕሬዚደንት የቃለ መሐላ ሥነ ስርዐት ላይ የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ፣የሜታው ማርክ ዘከርበርግ እና የቴስላ እና የቀድሞው ትዊተር የአሁኑ ኤክስ ባለቤት ኢላን መስክን ጨምሮ በርካታ አሜሪካዊያን ባለብዙ ቢሊዮን ዶላር ባለ ሀብቶች ላይ ተገኝተዋል። የቲክቶክ የሥራ አስፈጻሚ ሹ ዚ ቼውም እንዲሁ ተገኝተዋል። የቻይና ምክትል ፕሬዝደንት ሃን ዤንግ የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጆርጂያ መሎኒ እና የአርጀንቲናው ፕሬዝደንት ሃቪየር ሚሌ እና የኤኳዶሩ ዳኒየል ኖቦዋ ከተጋበዙት የውጭ መሪዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ዶናልድ ትረምፕ ከአራት ዓመታት በፊት ባሸነፏቸው በጆ ባይደን በዓለ ሲመት ላይ ሳይገኙ ከመቅረታቸውም ሌላ እስከዛሬ በዚያ ምርጫ በተፈጸመ በድምጽ መጭበርበር በድጋሚ እንዳልመረጥ ተደርጌአለሁ የሚለውን የሐሰት ውንጀላቸውን ገፍተውበታል። በዛሬው የእርሳቸው በዓለ ሲመት ላይ ግን የቀድሞዎቹ ፕሬዝዳንቶች ቢል ክሊንተን፣ ጆርጅ ደብሊው ቡሽ እና ባራክ ኦባማ ተገኝተዋል። Read more