newsare.net
በየአራት ዓመቱ እንደሚደረገው ሁሉ፣ በ2024ቱ ምርጫ አሸናፊ የሆኑት ዶናልድ ትረምፕ በትላንትናው ዕለት በዓለ ሲመታቸው ተከናውኗል። ትረምፕ በበዓለ ሲመታቸውየትረምፕ በዓለ ሲመት ንግግር ሲዳሰስ
በየአራት ዓመቱ እንደሚደረገው ሁሉ፣ በ2024ቱ ምርጫ አሸናፊ የሆኑት ዶናልድ ትረምፕ በትላንትናው ዕለት በዓለ ሲመታቸው ተከናውኗል። ትረምፕ በበዓለ ሲመታቸው ላይም ሆነ ከዛ በኋላ በነበሩት ፕሮግራሞች ላይ ንግግር አድርገዋል። በበዓለ ሲመታቸው ሥነ ስርዐት ላይ ባደረጉት ንግግር በርካታ የሃገር ውስጥ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ ጉዳዮችን አንስተዋል። አሜሪካ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ ስለሚኖራት ሚና፣ እንዲሁም አንዳንድ አወዛጋቢ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው የሚታመኑ ጉዳዮችን አንስተዋል። ትረምፕ ንግግራቸውን የጀመሩት “የአሜሪካ ወርቃማ ጊዜ ዛሬ ይጀምራል” ብለው ነበር። ደኅንነቷን፣ ሉአዓላዊነቷኣ እና ፍትህን እንድሚያስክብሩ ደጋግመው አውስተዋል። ኩሩ፣ የበለጸገና ነጻ ሃገር እንገነባለን ያሉት ትረምፕ፣ ከእርሳቸው በፊት የነበረው አስተዳደር የሃገሪቱን ደኅንነት እና ድንበር አልጠበቀም ሲሉ ነቅፈዋል። ሕገ ወጥ ወይም ሰነድ አልባ ስደተኞችን በተመለከተም በበዓለ ሲመታቸው ላይ አንስተዋል። ድንበሩን በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ እንደሚያሰጠብቁ ለዚህም የአሜሪካንን መከላከያ ኅይል እንደሚጠቀሙ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕገ ወጥ ፍልሰተኞችን ከሃገር እንደሚያስወጡ ተናግረዋል። ይህን ለማስፈጸምም በዚሁ በበዓለ ሲመታቸው ቀን የሥራ አስፈጻሚ ወይም ፕሬዝደንታዊ ትዕዛዝ ፈርመዋል። ሃገሪቱ ገጥሟታል ያሉትን ፈተናዎች ሁሉ እንደሚያሰወግዱ ቃል የገቡት ትረምፕ፣ ሃገራዊ አንድነትን ለማምጣት እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል። ትረምፕ በትላንትናው ዕለት ባደረጉት ንግግር በተወሰኑት ጉዳዮች ላይ የባለሞያ አስተያየት ጠይቀናል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more