newsare.net
የትዳር አጋሩን የተቆራረጠ አስከሬን በጀርባ በሚንጠለጠል ሻንጣ ውስጥ ይዞ ሲጓዝ የነበረን ግለሰብ መያዙን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል። የፖሊስ ዓባላት ግለሰበኬንያ የትዳር አጋሩን የተቆራረጠ አስከሬን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ግለሰብ ተያዘ
የትዳር አጋሩን የተቆራረጠ አስከሬን በጀርባ በሚንጠለጠል ሻንጣ ውስጥ ይዞ ሲጓዝ የነበረን ግለሰብ መያዙን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል። የፖሊስ ዓባላት ግለሰቡን የኮንትሮባንድ ሸቀጥ ይዟል በሚል ጥርጣሬ ሲፈትሹ የተቆራረጠ አስከሬን ማግኘታቸው ታውቋል። በምርመራ ወቅትም አስከሬኑ የ19 ዓመት ዕድሜ ያላት ባለቤቱ እንደኾነ የ 29 ዓመቱ ተጠርጣሪ ጃን ኪያማ ዋምቡዋ ለፖሊስ አስታውቋል። አሳዛኙ ሁኔታ የተሰማው በሴቶች ላይ የሚፈፀመውን ግድያ በመቃወምና ባለሥልጣናት ርምጃ እንዲወስዱ በመጠየቅ በመቶ የሚቆጠሩ ሴቶች በመዲናዋ ናይሮቢ ሰልፍ ባደረጉ በሳምንታት ውስጥ ነው። ፖሊስ ሰልፈኞቹን በአስለቃሽ ጋዝ በትኖ ነበር። ጃን ዋምቡዋ በተያዘበት ወቅት መረበሽ እንዳልታየበት ፖሊስ ጨምሮ አስታውቋል። ፖሊስ የዋምቡዋን ቤት የፈተሸ ሲሆን፣ ወለሉ እና ልብሶች በደም መለወሳቸውን አስተውሏል። ለግድያው የተጠቀመበት ሳይሆን አይቀርም የተባለ ስለታማ ቢላም ተገኝቷል። ተጨማሪ የአስከሬን አካላት ከአልጋ ሥር ማግኘቱንም ፖሊስ አስታውቋል ባለፈው ዓመት ዩጋንዳዊቷ ኦሊምፒክ ሯጭ ረቤካ ቼፕቴጂን ፍቅረኛዋ ነዳጅ አርከፍክፎ ማቃጠሉ ይታወሳል። አግነስ ቲሮፕ እና ዳማሪስ ሙትዋ የተባሉ ሴት አትሌቶችም በፍቅር አጋሮቻቸው መገደላቸው ይታወሳል። Read more