newsare.net
ቻይና በእንስሳት በሽታ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ከአፍሪካ፣ ከእስያ እና ከአውሮፓ ወደ ሀገሯ ይገባ የነበረውን የበግ፣ የፍየል እና የዶሮ ስጋ ምርት አገደች።ቻይና የበሽታ ስጋት ካለባቸው ሀገራት የእንስሳት ምርቶች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች
ቻይና በእንስሳት በሽታ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ከአፍሪካ፣ ከእስያ እና ከአውሮፓ ወደ ሀገሯ ይገባ የነበረውን የበግ፣ የፍየል እና የዶሮ ስጋ ምርት አገደች። ቻይን በማንኛውም ዐይነት የስጋ ምርት ላይ እገዳውን የጣለችው፣ የዓለም ጤና ድርጅት በተለያዩ ሀገራት የበሽታ ወረርሽኝ መከሰቱን የሚገልጽ መረጃ ይፋ ከአደረገ በኋላ መሆኑን፣ የቻይና ጉምሩክ መሥሪያቤት እ.አ.አ ጥር 21 ያወጣችው ተከታታይ ማስታወቂያ አመልክቷል። እገዳው የዓለማችን ትልቅ የስጋ አቅራቢ የሆኑትን እንደጋና፣ ሶማሊያ፣ ካታር፣ ኮንጎ፣ ታንዛኒያ፣ ግብፅ፣ ቡልጋሪያ፣ ምስራቅ ቲሞር እና ኤርትራን እንደሚያጠቃልል ተገልጿል። በተጨማሪም የበግ ስጋ፣ የፍየል ስጋ እና ሌሎች ተያያዥ ምርቶችን ከፓኪስታን፣ ፍልስጤም፣ አፍጋኒስታን፣ ኔፓል እና ባንግላዲሽ ማስገባት ማቆሟንም ቻይና አስትውቃለች። Read more