newsare.net
ዩናይትድ ስቴትስ የኮሎምቢያ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በምታካሂዳቸው በረራዎች ዙሪያ ሁለቱ ሀገራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ፣ አሜሪካ ኮአሜሪካ እና ኮሎምቢያ ስደተኞችን የማስወጣት ስምምነት ላይ ደረሱ
ዩናይትድ ስቴትስ የኮሎምቢያ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በምታካሂዳቸው በረራዎች ዙሪያ ሁለቱ ሀገራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ፣ አሜሪካ ኮሎምቢያ ላይ ልትጥል የነበረውን የአጸፋ ርምጃዎች ማንሳቷን ዋይት ሃውስ አስታውቋል። ዋይት ሃውስ ጉዳዩን አስመልክቶ በአወጣው መግለጫ፣ ኮሎምቢያ ስደተኞቿን ያለምንም ክልከላ እንደምትቀበል፣ ይህም በአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች እንዲመለሱ ማድረግን እንደሚጨምር ሁለቱ ሀገራት መስማማታቸውን አስታውቋል። የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ፔትሮ ቀደም ብለው ሁለት የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ሀገራቸው ላይ እንዳያልፉ ከልክለው የነበረ ሲሆን፣ ስደተኞችን የሚቀበሉት አሜሪካ በክብር እና በሲቪል አውሮፕላን አሳፍራ ስትልካቸው ብቻ ነው ብለው ነበር። ይህን ተከትሎ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኮሎምቢያ በሚገቡ ሸቀጦች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ እንደሚጥሉ እና በአንድ ሳምንት ውስጥ ውሳኔያቸውን ካልቀየሩ ወደ 50 ከመቶ እንደሚያድግ አስታውቀው ነበር። ቦጎታ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲም የቪዛ አገልግሎቱን እንዲያቋርጥ አድርገዋል። ኮሎምቢያ አዲሱን ስምምነት ካላከበረች አዳዲስ ቀረጦች እና ማዕቀቦች እንደሚጣልባትም የዋይት ኃውስ መግለጫ ጨምሮ አመልክቷል። ስደተኞችን ያሳፈረው የመጀመሪያው አውሮፕላን ኮሎምቢያ እስከሚያርፍ ድረስም፣ በቀደመው ክልከላ ምክንያት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኮሎምቢያ ባለስልጣናት ላይ የጣለው የቪዛ ማዕቀብ እና በጉምሩክ ፍተሻዎች ላይ የሚደረገው የተጠናቀረ ፍተሻ ባለበት እንደሚቆይ ዋይት ኃውስ አመልክቷል። ኮሎምቢያ በበኩሏ ሕዝቦቿን መብታቸው እና ሰብዓውነታቸው በተጠበቀ መልኩ እንደምትቀበል አስታውቃለች። Read more