newsare.net
ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው አየር ማረፊያ አቅራቢያ 60 መንገደኞችን የያዘ አንድ አውሮፕላንና አንድ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ረቡዕ ምሽት ተጋጭተው ፖቶማክ ወንዝ ውስከሄሊኮፕተር ጋራ የተጋጨው የአሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጓዦች በሙሉ አይተርፉም ተባለ
ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው አየር ማረፊያ አቅራቢያ 60 መንገደኞችን የያዘ አንድ አውሮፕላንና አንድ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ረቡዕ ምሽት ተጋጭተው ፖቶማክ ወንዝ ውስጥ ተከስክሰዋል። የአደጋ ሠራተኞች እስከ አሁን 28 አስከሬኖች ከወንዙ ማውጣቸውንም ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል። በአውሮፕላን ውስጥ የነበሩት ተሳፋሪዎች በሙሉ ሕይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉም ባለሥልጣናት ዛሬ ማለዳ አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት ሰዎችን በሕይወት ከማግኘት ወደ አስከሬን ፍለጋ ሥራ መሠማራታቸውን የዋሽንግተን ዲሲ የእሳት አደጋ መከላከያ ሃላፊ ጃን ዳናሊ አስታውቀዋል። “የሚተርፍ ሰው ይኖራል ብለን አናምንም” ብለዋል ኃላፊው። ስድሳ መንገደኞችን እና አራት ሠራተኞችን ይዞ ከካንሳስ የተነሳው የአሜሪካን አየር መንገድ አውሮፕላን በዋሽንግተን ሬገን አየር ማረፊያ ለማረፍ በመዘጋጀት ላይ ሳለ ነበር ሦስት ወታደሮችን ከያዘውና በሥልጠና ላይ ከነበረው ‘ብላክ ሆክ’ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ጋራ የተጋጨው። ከአደጋው የተረፉ እንዳሉ ለማግኘት ሦስት መቶ የሚሆኑ የአደጋ ሠራተኞችና ባሕር ሰርጓጆች ቀዝቃዛውን የፖቶማክ ወንዝ ውሃ ምሽቱን ሁሉ ሲያስሡ ቢያድሩም በሕይወት ያገኙት ሰው እንደሌለ ታውቋል። የአሜሪካ ብዙኅን መገናኛ በርካታ አስከሬኖች ከወንዙ ውስጥ መውጣታቸውን በመዘገብ ላይ ናቸው። ከተሳፋሪዎች ውስጥ የአሜሪካ ‘ፊገር ስኬቲንግ’ ወይም የበረዶ ላይ ትርዒት ስፖርት ቡድን ዓባላትና ቤተሰቦቻቸው እንደሚገኙበት የስፖርት ቡድኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ከእነዚህም ውስጥ ሁለቱ አሠልጣኞች ሩሲያዊ የቀድሞ የበረዶ ላይ ትርዒት የኦሎምፒክ አሸናፊዎች መሆናቸውን ክሬምሊን አረጋግጧል። Read more