newsare.net
ትላንት የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ከተማ ጎማን በአብዛኛው የተቆጣጠሩትና በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 አማጺያን፣ ወደ መዲናዋ ኪንሻሳ ግስጋሴያቸኤም 23 ወደ ኪንሻሳ እንደሚገሰግስ አስታወቀ
ትላንት የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ከተማ ጎማን በአብዛኛው የተቆጣጠሩትና በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 አማጺያን፣ ወደ መዲናዋ ኪንሻሳ ግስጋሴያቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። “የነጻነት ግስጋሴያችንን እንቀጥላለን ነው” ያለው የአማጺያኑ መግለጫ፡፡ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቺሰኬዲ በበኩላቸው ከበድ ያለ ወታደራዊ ምላሽ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል። አማጺያኑን የምትደግፈው ሩዋንዳ ፍላጎቷ በእ.አ.አ 1994 በሃገሪቱ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ላይ የተሳተፉ ተዋጊዎችን ለመደምሰስ እንደሆነ ብታስታውቅም፣ በማዕድን ሃብት ከበለጸገችው ኮንጎ ለዓለም የኤሌክትሮኒክስ ምርት ተፈላጊ ከሆነው ማዕድን ለማትረፍ ትሻለች የሚል ነቀፌታ ይቀርብባታል። “የነጻነት ግስጋሴያችንን እስከ ኪንሻሳ ድረስ እንቀጥላለን” ነው ያሉት ኤም 23ትን የሚጨምረው የአማጺያን ቅንጅት መሪ የሆኑት ኮርኔሊ ናጋ። በጎማ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት እንዲመለስ እንደሚያደርጉ የገለጹት የአማጺያኑ መሪ፣ የፀጥታ ጥበቃውም እንደሚደረግ ተናግረዋል። የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቺሰኬዲ ትላንት ለሃገሪቱ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር፣ አሸባሪ ብለው ለጠሯቸው አማጺያኑ ግስጋሴ “ጠንከር ያለና የተቀናጀ” ያሉት ወታደራዊ ምላሽ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። Read more