newsare.net
እስራኤል እና ሐማስ ዛሬ ሐሙስ ባደረጉት የእስረኞችና የታጋቾች ልውውጥ፣ ሶስት እስራኤላውያንና አምስት የታይላንድ ዜጎች የሚገኙበት ስምንት ታጋቾች መለቀቃእስራኤልና ሐማስ የእስረኛ እና ታጋች ልውውጥ አደረጉ
እስራኤል እና ሐማስ ዛሬ ሐሙስ ባደረጉት የእስረኞችና የታጋቾች ልውውጥ፣ ሶስት እስራኤላውያንና አምስት የታይላንድ ዜጎች የሚገኙበት ስምንት ታጋቾች መለቀቃቸውን የእስራኤል ሠራዊት አስታውቋል። በስምምነቱ መሠረት እስራኤል 110 ወታደሮችን ለቃለች፡፡ እስራኤላውያኑ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ እንዲገናኙ እንደሚደረግና የታይላንድ ዜጎችንም ከመግሥታቸው ጋራ እንደሚያገናኝ ሠራዊቱ ጨምሮ አስታውቋል። በተመሳሳይም 110 ፍልስጤማውያንን እስረኞችን የያዘ አውቶብስ ራማላህ፣ ዌስት ባንክ መድረሱ ታውቋል። በመቶ የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እስረኞቹን በደስታ ተቀብለዋል። ከተለቀቁት ውስጥ የቀድሞ የፍልስጤማውያን ወታደራዊ ቡድን መሪ ዘካሪያ ዙቤዲ እንደሚገኝበት ታውቋል። ዙቤዲ በእስራኤል ላይ በርካታ ሕይወትን የቀጠፉ ጥቃቶችን በማቀነባበር ይከሰሳል። Read more