newsare.net
በሶማሊያ የፑንትላንድ ባለሥልጣናት በቦሳሶ ከተማ የሚገኙና የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ሰነድ የሌላቸውን በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲያዙ አድርገዋል። ወፑንትላንድ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያንን ያዘች
በሶማሊያ የፑንትላንድ ባለሥልጣናት በቦሳሶ ከተማ የሚገኙና የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ሰነድ የሌላቸውን በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲያዙ አድርገዋል። ወደ ሀገራቸው እንደሚመልሱም አስታውቀዋል። እርምጃው ሰነድ አልባ የውጪ ዜጎችን ከሀገሪቱ የማስወጣት ዘመቻ አካል እንደሆነም ተመልክቷል። የተያዙት ስደተኞች በመኪና ተጭነው ከከማዋ ውጪ ተወስደዋል። ይህም ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በማሰብ ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል። እርምጃው የተወሰደው ፑንትላንድ በአይሲስ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ባልችበት ወቅት ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት አንድ በአይሲስ አባልነት የተጠረጠረን ግለሰብ የፀጥታ ኅይሎች ተኩሰው መግደላቸውን ተከትሎ ነው። የተያዙት ስደተኞች ከሽብር እንቅስቃሴ ጋራ ግንኙነት ይኖራቸው ባለሥልጣናት ማስረጃ አላቀረቡም። ዩሱፍ ሞሐመድ ዩሱፍ ያጠናቀረውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል። Read more