newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ የጦር አውሮፕላኖች በሶማሊያ የሚገኘውን እስላማዊ መንግሥት በመባል የሚታወቀው የአሸባሪ ቡድን ጋር ተያያዥ ያላቸውን ሽብርተኛ ቡድኖች ይዩናይትድ ስቴትስ በሶማሊያ የአይ ኤስ አሸባሪ ቡድን ጠንካራ ይዞታ ላይ ጥቃት ፈጸመች
የዩናይትድ ስቴትስ የጦር አውሮፕላኖች በሶማሊያ የሚገኘውን እስላማዊ መንግሥት በመባል የሚታወቀው የአሸባሪ ቡድን ጋር ተያያዥ ያላቸውን ሽብርተኛ ቡድኖች ይገኙበታል የተባለውን ተራራማ ምሽግ ላይ ፤ ጥቃት መፈጸማቸውን የሶማሊያ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች አስታውቀዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቅዳሜ ዕለት በማኅበራዊ ድረ-ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ጥቃቱ “ከፍተኛ የአይኤስ ጥቃት እና እቅድ አውጪ እንዲሁም አይ ኤስ የመለመላቸው እና የሚመራቸው አሸባሪዎች” ያነጣጠረ ዒላማ ነው ሲሉ ገልጸዋል። «ዩናይትድ ስቴትስን እና አጋሮቻችን የሚያስፈራሩትን እነዚህ አሸባሪዎች በዋሻ ውስጥ ተደብቀው አግኝተናቸዋል» ብለዋል ትራምፕ። አያይዘውም ጥቃቱ ሲቪሎችን ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያደርስ አሸባሪዎቹ ይኖሩባቸው የነበሩትን ዋሻዎች ሙሉ በሙሉ በማውደም ገድለዋል” ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግ ሴዝ በሰጡት የተናጥል መግለጫ ፤ ጥቃቱ በሶማሊያ ጎሊስ ተራሮች አካባቢ ላይ ያነጣጠረ ሲሆን «ጥቃቱ አይኤስ በአሜሪካ ዜጎች እና አጋሮቻችን እንዲሁም ንፁሀን ዜጎችን የሚያሰጉ የሽብር ጥቃቶችን የማሴር እና የማካሄድ አቅሙን አሳንሷል» ብለዋል። ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ጥቃቱ የተፈፀመው ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ጋር በመተባበር ነው ቢሉም ትራምፕም ሆነ ሄግ ሴዝ የአይኤስ እቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ዝርዝር አልሰጡም። የፑንትላንድ ጄኔራል አዳን አብዲ ሃሺ የአየር ጥቃቱ፤ የጎሊስ ተራሮች አካል በሆነው ካል ሚስካድ በተባለው አካባቢ፤ የእስላማዊ መንግስት ታጣቂዎች ላይ በሚገኙባቸው በትንሹ አስር የሚሆኑ ስፍራዎች ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል። በፑንትላንድ ባሪ ግዛት ቃንዳላ በተሰኘች ትንሽ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ በደህንነት ስጋት ምክንያት ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት አስተያየት፤ ከሩቅ የሚነሳ የጭስ እና የእሳት ነበልባል ማየታቸውን እና በትንሹ ሰባት የሚሆኑ ግዙፍ ፍንዳታዎች መስማታቸውን ተናግረዋል። የሶማሊያ ከፊል ራስ ገዝ ግዛት የሆነችው ፑንትላንድ ባለሥልጣናት በማህበራዊ መገናኛቸው፤ ተልዕኮው የተሳካ መሆኑን በመግለጽ ለዩናይትስ ስቴትስ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። Read more