newsare.net
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሁለቱ ጎረቤቶቻቸው ካናዳ እና ሜክሲኮ፣ እንዲሁም ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ አዲስ ቀረጥ ከጣሉ እና በምላሹትረምፕ አዲስ የቀረጥ ክፍያ የጣሉባቸውን የካናዳን እና የሜክሲኮን መሪዎችን ሊነጋገሩ ነው
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሁለቱ ጎረቤቶቻቸው ካናዳ እና ሜክሲኮ፣ እንዲሁም ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ አዲስ ቀረጥ ከጣሉ እና በምላሹ ሁለቱ አገሮች በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የአጻፋ ቀረጥ መጣላቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ከመሪዎቹ ጋር ለመነጋገር ማቀዳቸውን አመለከቱ። ትረምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው ከካናዳ እና ሜክሲኮ ጋር ተደራድረው ‘ነጻ-የንግግድ ስምምነት’ ተግባራዊ ቢያደርጉም፤ ከነገ ማክሰኞ አንስቶ ተፈጻሚ የሚሆን አዲስ የሃያ አምስት በመቶ ቀረጥ ሲጥሉባቸው፤ በቻይና ላይ ደግሞ ቀደም ሲል ከተደነገገው በተጨማሪ የአሥር በመቶ ቀረጥ ጥለዋል። ትረምፕ ሕገ-ወጥ ፍልሰትን ለማስቆም እና ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለብዙዎች ህልፈት ምክኒያት የሆነው ‘ፌንቲኔል’ የተባለ አደገኛ መድሃኒት ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ለመከላከል በቂ ጥረት አላደረጉም’ ሲሉ ሦስቱን ሃገራት ከሰዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዶናልድ ትረምፕ ትላንት ዕሁድ ማለዳ ላይ ‘ትሩዝ ሶሻል’ በተባለው የራሳቸው የማኅበራዊ ሚዲያ አውታር ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ በቀረጥ ጭማሪዎቹ የተነሳ አሜሪካውያን ሸማቾች ከፍተኛ የገበያ ዋጋ ጭማሪ ሊገጥማቸው እንደሚችል አምነዋል። በሌላ በኩል ለፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ ቀረጥ የሚከፍሉ የአሜሪካ ኩባንያዎች ከሌሎች ሃገራት ለሚያስገቧቸው የተለያዩ ምርቶች እና ሸቀጦች የሚጠየቁትን ተጨማሪ ወጭ ሙሉውን አለያም የሚበዛውን ወደሸማቹ ያሳፋሉ። “በአዲሱ ቀረጥ የተነሳ ጥቂት ቆንጠጥ የሚያደርግ ሕመም ሊኖር ይችላል?” ሲሉ ትረምፕ ራሳቸው ለሰነዘሩት ጥያቄ ሲመልሱ፡ “አዎን! ምናልባት! ሊኖርም ላይኖርም ይችላል! ነገር ግን አሜሪካን ዳግም ታላቅ እናደርጋለን። እናም ቢከፍሉት የማያስከፋ ዋጋ ይሆናል" ብለዋል። Read more