newsare.net
ዛሬ በዓመታዊው ‘ብሔራዊ የፀሎትና የቁርስ ሥነ ሥርዐት’ ላይ የተገኙት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ከተፈጸመባቸው ሁለት የግድያ ሙከራዎች በኋላከግድያ ሙከራዎች በኋላ ወደ ሃይማኖት መቅረባቸውን ትረምፕ ተናገሩ
ዛሬ በዓመታዊው ‘ብሔራዊ የፀሎትና የቁርስ ሥነ ሥርዐት’ ላይ የተገኙት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ከተፈጸመባቸው ሁለት የግድያ ሙከራዎች በኋላ ከሃይማኖት ጋራ ያላቸው ግንኙነት እንደተቀየረ አስታውቀዋል። አሜሪካዊያን “ፈጣሪን መልሠው በሕይወታቸው ውስጥ ያኑሩ” ሲሉ ጥሪ አድርገዋል ትረምፕ። በካፒቶል የሚካሄደውና የሰባ ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረው ዓመታዊ የፀሎትና የቁርስ ሥነ ሥርዐት የሁለቱም ፓርቲዎች የምክር ቤት ዓባላት የሚሳተፉበት ሃይማኖታዊ ሥነ ስርዓት ነው። “ከሃይማኖት ውጪ፣ ከእምነት ውጪ ደስተኛ መሆን እንደማይቻል አምናለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል ትረምፕ፡፡ ከግድያ ሙከራዎቹ በኋላ ወደ እግዚያብሄር ይበልጥ እንደቀረቡ ያመለከቱት ትረምፕ፣ ጆሯቸውን በጨረፈው ሙከራ ጸጉራቸው እንዳልተነካ ለዚህም ምስጋና ማቅረባቸውን ሲናገሩ ታዳሚውን ፈገግ አሰኝተዋል። ትረምፕና አስተዳደራቸው ከሃይማኖት መሪዎች ጋራ ግጭት ውስጥ ሲገቡ ከዚህ በፊት ተስተውሏል ያለው የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ፣ በባዕለ ሲመታቸው ቀን በተደረገ የቤተ ክርስቲያን ሥነ ሥርዓት ሰባኪው ማሪያን ቡደስ ለስደተኞችና ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ርህራሄ እንዲያሳዩ መጠየቃቸውን ትረምፕ ተቃውመው እንደነበር አመልክቷል። የካቶሊክ እምነት ተከታይ የሆኑት ምክትል ፕሬዝደንት ጄ ዲ ቫንስ ደግሞ የስደተኞችን ጉዳይ በተመለከተ ተመሳሳይ እምነት ካላቸው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋራ ሳይስማሙ ቀርተዋል። Read more