newsare.net
ደራሲ ሳልማን ሩሽዲን ኒው ዮርክ ውስጥ በተካሄደ በአንድ ትምህርታዊ ስብሰባ ላይ ሳለ በቢላ ወግቶ ለመግደል የሞከረው ግለሰብ የፍርድ ቤት ሂደት ዛሬ ሲጀመር፣ የሳልማን ሩሽዲን በስለት ለመግደል የሞከረው ግለሰብ የፍርድ ቤት ሂደት ጀመረ
ደራሲ ሳልማን ሩሽዲን ኒው ዮርክ ውስጥ በተካሄደ በአንድ ትምህርታዊ ስብሰባ ላይ ሳለ በቢላ ወግቶ ለመግደል የሞከረው ግለሰብ የፍርድ ቤት ሂደት ዛሬ ሲጀመር፣ የከሳሽ ጠበቆች የመክፈቻ ክርክራቸውን ማሰማት ጀምረዋል። ሩሽዲ በፍርድ ቤቱ እንዲመሰክር የሚጠበቅ ሲሆን፣ በመግደል ሙከራ ከተከሰሰው ሃዲ ማታር ጋራ ከጥቃቱ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ይገናኛል ተብሏል። ከሁለት ዓመታት በፊት በኒው ዮርክ በተዘጋጀና ደራሲያን ደኅንነታቸውን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው ባተኮረ ስብሰባ ላይ በመናገር ላይ ሳለ ነበር ሃዲ ማታር ወደ መድረኩ በመሄድ ሩሽዲን ከ12 ጊዜ በላይ በበርካታ የሰውነቱ ክፍሎች ላይ በቢላ የወጋው። ጥቃቱ ሩሽዲን በከፊል ማያት የተሳነው እንዲኾን ሲያደርግ አንድ እጁ ላይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ትውልዱ ከህንድ የሆነውና የአሜሪካና የእንግሊዝ ጥምር ዜግነት ያለው ሩሽዲ፣ በጥቃቱ ላይ ያተኮረ ግለ ታሪክ መጽሓፍ ባለፈው ዓመት አሳትሟል። ሩሽዲ በእ.አ.አ 1989 ያሳተመውና “ሳታኒክ ቨርስስ” የተሰኘው መጽሐፍ እስልምናን የሚያንቋሽሽ ነው በሚል በበርካታ የሃይማኖቱ ተከታዮች ይወገዛል። የኢራኑ አያቶላ ኾሚኒም ሩሽዲ እንዲገደል ፋትዋ አውጥተው ነበር። ኢራን ትዕዛዙን እንደማትፈጽም መግለጿን ተከትሎ ለረጅም ጊዜ ተደብቆ የነበረው ሩሽዲ እንደልብ መዘዋወር ጀምሮ ነበር። Read more