newsare.net
ከልጅነቱ ጀምሮ አንድ እግሩ አልታዘዝ ያለው መለስ እዮብ፣ አካል ጉዳተኛ መኾኑ ሌሎች መደገፊያ ያጡ አካል ጉዳተኛ ኢትዮጵያውያን ከመርዳት አላገደውም። ከብዙአካል ጉዳተኛ መኾኑ ለሌሎች መደገፊያ ከመሥራት አላገደውም
ከልጅነቱ ጀምሮ አንድ እግሩ አልታዘዝ ያለው መለስ እዮብ፣ አካል ጉዳተኛ መኾኑ ሌሎች መደገፊያ ያጡ አካል ጉዳተኛ ኢትዮጵያውያን ከመርዳት አላገደውም። ከብዙ ዓመታት በፊት አንድ መንግሥታዊ ያልኾነ ድርጅት በሰጠው ክራንች ድጋፍ ያደገው መለስ፣ አንድ ቀን ድጋፉ በመሰበሩ ወድቆ ዳግም ተጎድቶ እንደነበር ያስታውሳል። በወቅቱ የነበረው ሁኔታም ለሌሎች በተመሳሳይ ችግር ውስጥ ለሚያልፉ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል አዲስ ነገር ማቋቋም እንዳለበት እንደወሰነ ገልጿል። ሆስፒታል ተቀጥሮ በመሥራት ያገኘውን ገንዘብ አጠራቅሞና፣ ከጓደኞቹ ያገኘውን ጨምሮ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ድጋፍ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል። ] በዚህ ዙሪያ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more