newsare.net
አሜሪካ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ከእስላማዊ መንግሥት ጋራ ግንኙነት አላቸው የተባሉ 16 ነውጠኞችን መግደሏን የሶማሊያ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። በፑንትላአሜሪካ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 16 ነውጠኞች መገደላቸውን ሶማሊያ አስታወቀች
አሜሪካ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ከእስላማዊ መንግሥት ጋራ ግንኙነት አላቸው የተባሉ 16 ነውጠኞችን መግደሏን የሶማሊያ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። በፑንትላንድ የጸጥታ ዘመቻዎች ቃል አቀባይ የሆኑት ብርጋዴር ጄነራል ሞሃሙድ አህመድ ለቪኦኤ የሶማሊኛ ቋንቋ አገልግልግሎት እንዳስታወቁት፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት የሟቾቹን ዜግነት ለማጣራት በመሥራት ላይ ናቸው። በእሑድ የአየር ጥቃት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ቁልፍ ሚና እንደተጫወተች ጀኔራሉ አስታውቀዋል። በአየር ጥቃቱ ወቅት ነውጠኞቹ በፑንትላን የፀጥታ ኅይሎች መሠረት ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸማችውን ጀኔራሉ ጨምረው አስታውቀዋል። በአፍሪካ የአሜሪካ ዕዝ ቀደም ብሎ በአወጣው መግለጫ፣ የአየር ጥቃት መከናወኑንና ሁለት ሽብርተኞች መገደላቸውን አስታውቆ ነበር። በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ፣ የአየር ጥቃቱ ሀገራቸውና አሜሪካ ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት ያላቸውን ጠንካራ አጋርነት የሚያሳይ ነው ብለዋል። የእሁዱ ጥቃት አሜሪካ በአንድ ወር ውስጥ የፈጸምችው ሁለተኛው የአየር ጥቃት ነው። ከበርካታ ወራቶች ዝግጅት በኋላ ፑንትላንድ በአካባቢው በሚገኙ ሽብርተኞች ላይ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ነች፡፡ ከ200 በላይ የአይሲስ ተዋጊዎችን መግደሏንና ከእነዚህም ውስጥ በርካታ የውጪ ዜጎች እንደሚገኙበት ፑንትላን አስታውቃለች፡፡ Read more