newsare.net
ከፍተኛ የአሜሪካ እና የሩሲያ ዲፕሎማቶች፣ በሀገሮቻቸው መካከል ስላለው ግንኙነት እና በዩክሬን ያለው ጦርነት ሊያቆም በሚችልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር በዛሬውየዩናይትድ ስቴትስ እና የሩሲያ ባለሥልጣናት በዩክሬን ጦርነት እና ሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ለመወያየት ተገናኙ
ከፍተኛ የአሜሪካ እና የሩሲያ ዲፕሎማቶች፣ በሀገሮቻቸው መካከል ስላለው ግንኙነት እና በዩክሬን ያለው ጦርነት ሊያቆም በሚችልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር በዛሬው ዕለት ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ስብሰባ ጀምረዋል። ንግግሮቹ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን የፊት ለፊት ውይይት ያደርጉ ዘንድ የሚያስችሉ የመነሻ ርምጃዎች መሆናቸውን በመግለጽ ሁለቱም ወገኖች በውይይታቸው ዙሪያ ሲሰጡ ለነበሩ መላምቶች ምላሽ ሰጥተዋል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ ማርኮ ሩቢዮ ፣የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ማይክ ዋልትዝ እና የመካከለኛው ምስራቅ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊኮፍ የሚገኙበትን ልዑክ መርተዋል። በሩሲያ በኩል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ እና ከፍተኛው የፑቲን ረዳት ዩሪ ዩሻኮቭ ተገኝተዋል። የዩክሬን መሪዎች በውይይቱ ለመሳተፍ እንዳልተጋበዙ ተናግረዋል። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የዩክሬን ልዑክ ኪት ኬሎግን ዕረቡ ዕለት አግኝተው ያነጋግራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዩክሬን በራሷ ዕጣ ፋንታ ዙሪያ በሚደረጉ ውይይቶች መሳተፍ እንዳለባት እና በቀጠናቸው ደህንነት ዙሪያ እንደ አዲስ ለውጥ በተመለከቱት ጉዳይ ላይ የበኩላቸውን ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ በቅርቡ ይፋ ባደረጉት የአውሮፓ መሪዎች ዘንድ አዲሱ የዩኤስ-ሩሲያ ግንኙነት ስጋት ፈጥሯል። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የአውሮፓ መሪዎችን ቡድን ሰኞ ዕለት ፓሪስ ላይ ስብሰባ ጠርተው የመከላከያ ወጪን ስለማሳደግ እና ለዩክሬን ሊሰጡ በሚገቡ የጸጥታ ዋስትናዎች ዙሪያ ተወያይተዋል። የፈረንሳዩ መሪ ከፓሪሱ ውይይት በኋላ ከትረምፕ እና ዜለንስኪ ጋር መነጋገራቸውን ገልጸው አውሮፓውያን፣ አሜሪካውያን እና ዩክሬናውያን በጋራ መሥራታቸው አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። «ጠንካራ እና አስተማማኝ» የደኅንነት ዋስትናዎች እንደሚያስፈልጉ የተናገሩት ዜለንስኪ፣ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ሩሲያ ከዩክሬን ወይም ከሌሎች የአውሮፓ አገሮች ጋራ ሌላ ጦርነት እንደምትጀምር አክለው ገልጸዋል። Read more