newsare.net
የጀርመን መራጮች ዛሬ እሁድ በሚካሄደው ምርጫ ድምፅ መስጠት ጀምረዋል። ምርጫው ለዓመታት የተቀዛቀዘው የአውሮፓ ኢኮኖሚ፣ ስደትን ለመግታት የሚደረገው ጫና፣ኢኮኖሚ፣ ስደት እና አክራሪ ኃይሎች ትኩረት የሳቡበት የጀርመን ምርጫ እየተካሄደ ነው
የጀርመን መራጮች ዛሬ እሁድ በሚካሄደው ምርጫ ድምፅ መስጠት ጀምረዋል። ምርጫው ለዓመታት የተቀዛቀዘው የአውሮፓ ኢኮኖሚ፣ ስደትን ለመግታት የሚደረገው ጫና፣ የዩክሬን ዕጣ ፈንታ እና ስጋት ውስጥ የወደቀው የአውሮፓ እና የዩናይትድ ስቴትስ አጋርነት ጥላ ያጠላበት ነው። ለዘብተኛ ቀኝ ዘመም ተቃዋሚዎች ምርጫውን ሊያሸንፉ ይችላሉ የሚሉ ግምቶች ቢኖሩም፣ ከሕዝብ የተሰበሰቡ ድምፆች በበኩላቸው፣ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ባልታየ ሁኔታ ለቀኝ አክራሪ ፓርቲ ድጋፍ እንዳለ አሳይተዋል። ጀርመን ከ27ቱ የአውሮፓ ህብረት አባላት በሕዝብ ብዛት ቀዳሚዋ ስትሆን፣ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ)ም ከፍተኛውን ድርሻ ትይዛለች። ከዩናይትድ ስቴትስ ቀጥሎ ለዩክሬን ከፍተኛ የጦር መሳሪያ አቅራቢ በሆነችው ጀርመን እስካሁን ከህዝብ የተሰበሰቡ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት፣ የለዘብተኛው ቀኝ ዘመም የተቃዋሚ መሪ ፍሬድሪክ ሜርዝ ፓርቲ ከ28-32 በመቶ ድጋፍ ሲያገኝ የቆየ ሲሆን ሜርዝ፤ ሾልዝን ሊተኩ ይችላሉ ተብሎም ተገምቷል። የፀረ-ስደት አቋም የሚያራምደው ቀኝ አክራሪው ኤ ኤፍ ዲ የተሰኘው ፓርቲ በበኩሉ በ20 ከመቶ ድምፅ በሁለተኛነት ሲከተል ቆይቷል። በዛሬው የጀርመን ምርጫ የሚፎካከሩት ፓርቲዎች በዋናነት ላለፉት ሁለት አመታት ያሽቆለቆነውን የጀርመን ኢኮኖሚ በድጋሚ እንዲያንሰራራ ያስችላል ያሉትን ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን፣ ባለፈው ወር በስደተኞች የተፈጸሙትን ጥቃቶች ተከትሎም፣ የስደት ጉዳይ የምርጫ ዘመቻው ቀዳሚ አጀንዳ መሆን ችሏል። Read more