newsare.net
የአይሲሲ ዐቃቤ ሕግ ካሪም ካን በምስራቃዊው የአገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ተባብሶ ከቀጠለባት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ መግባታቸውን ጽሕፈየዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ጠበቆች ግጭት ካየለባት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ገቡ
የአይሲሲ ዐቃቤ ሕግ ካሪም ካን በምስራቃዊው የአገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ተባብሶ ከቀጠለባት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ መግባታቸውን ጽሕፈት ቤታቸው ዛሬ አስታወቀ። በሩዋንዳ የሚታገዘው ኤም 23 በቅርቡ ምስራቃዊ ኮንጎ ውስጥ ሁለት ትልልቅ ከተሞችን በቁጥጥር ስር በማዋል አማጺው ቡድን ነፍጥ ካነሳበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2021 መገባደጃ ወዲህ በቀጣናው ግዙፍ ሥፍራ እንዲኖረው አድርጎታል። ካን ዋና ከተማይቱ ኪንሻሳ እንደደረሱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኮንጎ ውስጥ እየሆነ ያለው ሁኔታ፤ በተለይም በምስራቃዊው የሃገሪቱ ክፍል የሚካሄደው ግጭት በእጅጉ አሳሳቢ መኾኑን እንረዳለን” ብለዋል። “መልዕክቱ በግልፅ መተላለፍ አለበት። የትኛውም የታጠቀ ቡድን፣ የትኛውም የታጠቀ ኃይል፣ እና የትጥቅ አጋር የሆነ ወገን፤ በመካሄድ ላይ ካለው ምርመራ እና ከተጠያቂነት ነጻ አይሆንም” ብለዋል። «ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕጎችን ማክበር አለባቸው» ሲሉም አክለዋል ካን። እንደ መንግሥታቱ ድርጅት ባለሞያዎችም ገለጻም አማጺው ቡድን ኤም 23 ቁጥራቸው 4 ሺሕ በሚጠጉ የሩዋንዳ ወታደሮች ይደገፋል። Read more