newsare.net
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ባለፈው ታኅሣሥ ወር መጀመሪያ በቱርክ ፕሬዝደንት ረሽፕ ታይፕ ኤርዶዋን አሸማጋይነት የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የኹለቱ ሀገጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሊያ ጉብኝት አደረጉ
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ባለፈው ታኅሣሥ ወር መጀመሪያ በቱርክ ፕሬዝደንት ረሽፕ ታይፕ ኤርዶዋን አሸማጋይነት የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የኹለቱ ሀገራት ግንኙነት እየተሻሻለ ባለበት ወቅት፣ ወደ ሞቃዲሾ ያቀኑት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፕሬዝደንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድና በሌሎች የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ረፋዱ ላይ ለይፋዊ ጉብኝት ሞቃዲሹ እንደደረሱ፣ የአል ሻባብ እንደኾነ የተገመተ በርካታ ዙር የሞርታር ተኩስ ወደ አውሮፕላን ማረፊያው አቅጣጫ መከፈቱን በደኅንነት ስጋት ምክንያት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ቢያንስ አንዱ የሞርታር ተኩስ በአውሮፕላን ማረፊያው ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኝ ጋራዥ ውስጥ ማረፉን ደግሞ ስሙ ያልተጠቀሰ የተቋሙ ባልደረባ ገልጿል። የሞርታር ጥቃቱን ተከትሎ የደረስ ጉዳት እንደሌለም ታውቋል። በሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድ አቀባበል የተደረገላቸው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ፕሬዝደንታዊ ቤተ መንግሥት ተወስደው ሁለቱ ወገኖች ውይይት አድርገዋል። ዛሬ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ሞቃዲሹ የገቡት ዐቢይ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። ሁለቱ ወገኖች ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ባለፉት ጥቂት ወራት ሲካሄዱ የቆዩ ተከታታይ ግንኙነቶች ቀጣይ መኾኑን ጠቅሰው፣ በኹለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደነበረበት የመመለሱን ሂደት ይበልጥ ያጠናክራል ሲሉ አክለዋል ። ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋራ የባሕር ሠፈር በሊዝ ለማግኘት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ በኹለቱ ወገኖች መካከል የነበረው ግንኙነት ባለፈው አንድ ዓመት ሻክሮ ቆይቷል። ጉብኝቱ፣ 2ሺሕ 500 የኢትዮጵያ ወታደሮችን በአፍሪካ ኅብረት ልዑክ ውስጥ ለማካተት የኹለቱ ሀገራት ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣናት በቅርቡ መስማማታቸውን ተከትሎ የተደረገ ነው። በኹለቱ ሀገራት መካከል ባለው ወታደራዊ ስምምነት መሠረትም፣ በአፍሪካ ኅብረት ከሚሳተፉት ውጪ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ወታደሮችንም በሶማሊያ ታሰማራለች፡፡ መሪዎቹ በከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ስምምነት ላይ መደረሱን በመልካም መቀበላቸውን ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል። ሁለቱ መሪዎች በተጨማሪም “በተጠናከረ ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ትብብር መተማመንን ማስፈን አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል” ሲል የጋራ መግለጫው አክሏል። ዲፕሎማሲያዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ትብብርን በማሳደግ መተማመንን መገንባት እንደሚያስፈልግ ኹለቱ መሪዎች አጽንኦት መስጠታቸውንም የጋራ መግለጫው አመልክቷል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፣ሁለቱ መሪዎች ከዚህ ቀደም ካደረጓቸው ውይይቶች የቀጠለ ሰፋ ያለ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቋል። ውይይታቸው «በሰላም እና ፀጥታ፣ በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ እና በጋራ ሊሠሩ በሚችሉ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ ያተኮረ ነበር » ብሏል። Read more