newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በእቅዳቸው መሰረት በመጪው ሳምንት ከካናዳ እና ከሜክሲኮ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ እንደሚጥሉ አስታትራምፕ በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይና ላይ ዐዳዲስ ቀረጦች ሊጥሉ ነው
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በእቅዳቸው መሰረት በመጪው ሳምንት ከካናዳ እና ከሜክሲኮ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ እንደሚጥሉ አስታወቁ። ትራምፕ ይህን ውሳኔያቸውን የሚተገብሩት ሁለቱ ጎረቤት ሀገራት አሁንም ወደ አሜሪካ የሚገቡትን የአደንዛዥ ዕፅ ፍሰት ለመግታት በቂ ጥረት አላደረጉም በማለት ነው። ትራምፕ አክለው በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ቻይና ላይ ከጣሉት 10 ከመቶ ቀረጥ በተጨማሪ ከመጪው ማክሰኞ ጀምሮ ሌላ 10 በመቶ ቀረጥ እንደሚጥሉ ትሩዝ በተሰኘው የማኅበራዊ ሚድያቸው ላይ አስታውቀዋል። ቻይና የመጀመሪያውን የትራምፕ ቀረጥ ተከትላ ከአሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ ተመሳሳይ ቀረጥ ጥላ ነበር። «አሁንም ከሜክሲኮ እና ካናዳ አደንዛዥ ዕፆች ወደ ሀገራችን እየጎረፉ ነው» ያሉት ትራምፕ «ከነዚህ መድኃኒቶች ውስጥ አብዛኞቹ በቻይና ተመርተው የሚቀርቡ ፈንተነል ናቸው» ብለዋል። ትራምፕ በቅርብ አጋሮቻቸው ካናዳ እና ሜክሲኮ ላይ ቀረጥ እንደሚጥሉ ያስታወቁት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ቢሆንም፣ የሜክሲኮ ፕሬዝደንት ክላውዲያ ሼንበም አደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን ለመቆጣጠር 10 ሺሕ ወታደሮችን ወደ ሀገራቸው ሰሜናዊ ድንበር እንደሚልኩ መናገራቸውን ተከትሎ ውሳኔያቸውን አዘግይተዋል። የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶም ጉዳዩን ለመፍታት «የፈንተነል ተቆጣጣሪ» እንደሚሰይሙ ተናግረው ነበር። 80 ከመቶ የውጭ ንግዳቸውን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚልኩት ሼንበም በዚህ ሳምንት መጀመሪያ፣ ከአሜሪካ ጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ እየጠበቁ መኾኑን እና ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻሉ ግን ሜክሲኮ በአሜሪካ ምርቶች ላይ ተመሳሳይ ቀረጥ እንደምትጥል አስታውቀው ነበር። Read more