newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ እና የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮለድሚር ዜለንስሊ ውይይት ወደ ተጋጋለ እሰጥ አገባ ከተቀየረ እና ትረምፕ ዜለንስኪንከትረምፕ እና ዜለንስኪ የተጋጋለ እሰጥ አገባ በኋላ የአውሮፓ መሪዎች ከዩክሬን ጎን ቆመዋል
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ እና የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮለድሚር ዜለንስሊ ውይይት ወደ ተጋጋለ እሰጥ አገባ ከተቀየረ እና ትረምፕ ዜለንስኪን «አክብሮት የጎደለው» ሲሉ ከተናገሯቸው በኋላ በመላ አህጉሪቱ የሚገኙ የአውሮፓ መሪዎች ከዩክሬን ጎን ቆመዋል። የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ካጃ ካላስ ፣ «አኹን ነጻው ዓለም አዲስ መሪ እንደሚያስፈልገው ግልጽ ኾኗል» ብለዋል። በዚኹ በማኅበራዊ ሚዲያ ኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጹሑፍ፣ «ዩክሬን የአውሮፓ ነች፣ ከዩክሬን ጎን እንቆማለን» ብለዋል። የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ «ዩክሬን በጀርመን ላይ መተማመን ትችላለች - በአውሮፓም ላይ እንዲኹ» በማለት ኤክስ ላይ ሲጽፉ፣ የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ደግሞ «ዩክሬን- ስፔን ከጎንሽ ትቆማለች” ብለዋል። የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ቱስክ »ውድ ዜለንስኪ እና ውድ የዩክሬን ጓደኞቻችን ፣ ብቻህን አይደለህም« ሲሉ በኤክስ ላይ ጽፈዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በበኩላቸው ለፖርቹጋል ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ »አጥቂዋ ሩሲያ ነች። ተጠቂው የዩክሬን ሕዝብ ነው” ብለዋል። የፊንላንድ፣ ኔዘርላንድስ፣ ቼክ ሪፐብሊክ እና ኖርዌይን ጨምሮ ሌሎች የአውሮፓ መሪዎችም ለዩክሬን ድጋፋቸውን ለመስጠት በማኅበራዊ ገጾቻቸው ላይ ጽፈዋል። ኖርዌይም በማኅበራዊ ሚዲያ ለዩክሬን ድጋፏን ገልጻለች። ሆኖም ዩክሬንን የደገፉት ሁሉም የአውሮፓ መሪዎች አይደሉም፣ ለኪቭ የሚሰጠውን ርዳታ ለረዥም ጊዜ ሲቃወሙ የቆዩት የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን፣ ምንም እንኳን ሁኔታውን ለሌሎች ለመቀበል ቢከብዳቸውም ፕሬዝደንት ትረምፕ ለሰላም የቆሙ ናቸው። እናመሰግናለን ፕሬዝደንት!” ብለው ጽፈዋል። Read more