newsare.net
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በግጭት ወቅት የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶች ጉዳይ ልዩ ተወካይ ፣”በዓለም አቀፍ ደረጃ ወታደራዊ ወጪ እያደገ ሲሄድ ፣ ግጭት ይጨምራልየለጋሾች ድጋፍ በመቀነሱ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አዲስ የርዳታ ምንጭ እየፈለጉ ነው
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በግጭት ወቅት የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶች ጉዳይ ልዩ ተወካይ ፣”በዓለም አቀፍ ደረጃ ወታደራዊ ወጪ እያደገ ሲሄድ ፣ ግጭት ይጨምራል፡፡ በዚያ ደግሞ በዋናነት የሚጎዱት ሴቶች እና ህጻናት ናቸው« ሲሉ ተናገሩ። ኮሎምበስ ማቭሁንጋ እንደዘገበው፣ በግጭት ቀጣና ውስጥ ያለውን ስቃይ ለማስታገስ የሰብአዊ ረድዔት ድርጅቶች፣ እንደ ሳዑዲ አረቢያ ያሉ ከተለመዱት የተለዩ አዳዲስ የገንዘብ ድጋፍ ምንጮችን በመፈለግ ላይ ናቸው። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በግጭት ውስጥ የሚፈጸሙ የፆታዊ ጥቃቶች ጉዳይ ልዩ ተወካይ ፕራሚላ ፓተን በሪያድ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ርዳታ መድረክ ላይ ለቪኦኤ ሲናገሩ “ዓለም አቀፋዊ ግጭቶች በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ” እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል፡፡ »እያየን ያለነው በግጭቶች ወቅት ፆታዊ ጥቃት በብዛት እንደሚፈጸም ነው፣” ያሉት ፓተን “ በዚህ ደግሞ ሰላማዊ ዜጎች በሙሉ በጣም ይጎዳሉ፣ በይበልጥ የሚጎዱት ግን ሴቶች እና ልጃገረዶችው። በመከላከል ላይ የበለጠ መሥራት ይኖርብናል። መገለልን፣ ድህነትን፣ የፆታ እኩልነት መዛባትን ዋና መንስኤ ለመፍታት መሥራት አለብን። በእርግጥ ምላሽ መስጠት ይኖርብናል፣ መከላከል ግን ላይ የበለጠ መሥራት ያለብን ይመስለኛል።” ብለዋል። በተባበሩት መንግሥታት ስር ያሉና በሳዑዲ አረብያ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የተሳተፉ ብዙ የሰብአዊ ቡድኖች ነባሮቹ «የምዕራባውያን» ለጋሾች የገንዘብ ድጋፋቸውን ቀንሰዋል ወይም አቁመዋል ሲሉ ተናግረዋል። ምንም እንኳን በፍርድ ቤቶች በኩል ሕጋዊ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙትም፣ የትረምፕ አስተዳደር በብዙ 10 ቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር የውጭ ርዳታን ለማቁረጥ ተንቀሳቅሷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የዩኒሴፍ የተመድ የህጻናት እርዳታ ድርጅት አቅርቦት ክፍል ዳይሬክተር ሌይላ ፓካላ ተቋማቸው “ከ109 ሚሊዮን በላይ ተጋላጭ ህጻናትን እና ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት 9.9 ቢሊዮን ዶላር እየፈለገ ነው” ብለዋል። «በዚህ ዓመት በሰብአዊነት ዙሪያ የሚያስፈልገውን ሁሉ ስንመለከት በአመጋገብ ይሁን፣ በውሃ እና በንፅህና አጠባበቅ ይሁን፣ በጤና ተደራሽነት፣ እና ህጻናት ክትባት እንዳያጡ ለማድረግ ተጨማሪ ፍላጎቶች መኖራቸውን እንመለከታለን፣ “ ሲሉ ፓካላ ያለው አቅም ከፍላጎቶች ጋር እየተራመደ እንዳልሆነም አክለዋል። ፓካላ አያይዘውም »በዓለም ዙሪያ በከባድ አጣዳፊ የምግብ እጦት የሚሰቃዩ ህጻናት ቁጥር እየጨመረ ነው። በግጭት ዞኖች እና ያልተረጋጉ ሁኔታዎች ወይም በደቡባዊ አፍሪካ እንዳየነው በማያቋርጥ ድርቅ ፣ ጎርፍ እና የከባድ አውሎ ነፋስ በመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎች፣ በሚሰጥ የመጀመሪያው አጣዳፊ ምላሽ እጥረት ህጻናትና ቤተሰቦች እየተጎዱ ነው።” በማለት “ያለው ፍላጎት ምላሽ ከመስጠት አቅም በላይ ነው።” ብለዋል። ኤስ.ኦ. ኤስ ኢንተርናሽናል የህፃናት መንደር የተባለው ለትርፍ ያልተቋቋመው ድርጅት ፕሬዝደንት፣ ደረጀ ወርዶፋ፣ “የአየር ንብረት ለውጥ ለአጠቃላዩ ሰብአዊ ቀውስ አስተዋፅዖ እያደረገ ነው” ይላሉ።“ሁኔታው “በተለይም በምስራቅ እና በደቡባዊ አፍሪካ እየተባባሰ ነው። ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ በሰብአዊ ቀውስ የተጎዱ ብዙ ሰዎች አሉ። “ የሚሉት ደረጀ “ለእነዚህ የተጎዱ ማኅበረሰቦች አገልግሎቶችን እና ቁሳቁሶችን ለማምጣት የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን በጣም በጣም ከፍተኛ ነው። የዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድጋፍ ወደዚህ ደረጃ እና የፍላጎት መጠን እየመጣ አይደለም” ይላሉ። አንዳንድ ቡድኖች የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ፊታቸውን ወደ ሳዑዲው- የንጉሥ ሳልማን የሰብአዊ እና የአስቸኳይ ርዳታ ማእከል (KSRelief) ወደ መሳሰሉ ድርጅቶች ፊታቸውን እያዞሩ ነው። የዚህ ድርጅት (KSRelief) የአጋርነት እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ሃና ኦማር፣ “ግጭቶች እና የአየር ንብረት ለውጥ ብዙ ሰዎችን ለችግር መዳረጉን” ገልጸው፣ ድርጅቱ ብዙ የአፍሪካ ሀገራትን እየረዳ ነው ይላሉ። ኦማር አክለውም “ርዳታ ለማድረስ፣ ለእነዚህ ሰዎች መብት የምንሟገትበትን መንገዶች ለመፈለግ እና ለተቸገሩት መድረሳችንን ለማረጋገጥ ቁርጠኞች ነን። ሰዎች አሁንም እነዚህን ሁሉ ተግዳሮቶች ለመፍታት እና መፍትሄዎችንም እንደሚፈልጉ ተስፋ አለ።” ብለዋል። በዚህ ዓመት ድርጅቱ (KSRelief) ከሳውዲ አረቢያ ውጪ የሰብአዊ ሥራውን የጀመረበትን 10ኛ ዓመት ሲያከብር “የሰብአዊ ምላሽን የወደፊት እጣ ፈንታን ማሰስ” በሚል መሪ ቃል ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር የሰአብ አዊ ውይይት መድረክ አዘጋጅቷል። Read more