newsare.net
ቻይና የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የሚያስችሏትን ፕሮጀክቶች እንደምታዘጋጅ ዛሬ ረቡዕ አስታውቃለች። ፕሮጀክቶቹ እ.አ.አ ከ2030 አስቀድማ የካርበን ዳይኦክቻይና የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም ትላልቅ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች ማቀዷን ይፋ አደረገች
ቻይና የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የሚያስችሏትን ፕሮጀክቶች እንደምታዘጋጅ ዛሬ ረቡዕ አስታውቃለች። ፕሮጀክቶቹ እ.አ.አ ከ2030 አስቀድማ የካርበን ዳይኦክሳይድ በካይ ጋዝ ልቀቷን መጠን በመገደብ በ2060 ደግሞ ከካርበን ልቀት ነፃ የሚያደርጋት መሆኑን አመልክታለች። ሙቀት አማቂ ጋዞችን በብዛት ወደ አየር በመልቀቅ ከዓለም ቀዳሚ የሆነችው ቻይና፣ በባሕር ዳርቻዎች ላይ አዳዲስ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን እንደምታለማ እና በበረሃማ አካባቢዎች «አዳዲስ የኃይል መሠረተልማቶችን» እንደምትገነባ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እቅድ አውጪ ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። ሪፖርቱ አክሎ «ቻይና የካርበን ልቀትን ለመቀነስ እና በሂደት ሙሉ ለሙሉ ለማቆም በንቃት እና በጥንቃቄ ትሰራለች» ብሏል። ሆኖም በሀገሪቱ የድንጋይ ከሰል ቁልፍ የኃይል ምንጭ ሆኖ እንደሚቀጥል ያመለከተው ሪፖርቱ፤ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችን እያቀደች ባለችበት ወቅትም በዚህ ዓመት የድንጋይ ከሰል ምርትና አቅርቦትን ማሳደጓን እንደምትቀጥል ገልጿል። Read more