newsare.net
በጋምቤላ ክልል በኑዌር ዞን በተከሠተው የኮሌራ ወረርሽኝ፣ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ30 በላይ ሰዎች መሞታቸውንና ከአንድ ሺሕ በላይ የሚደርሱ ደግሞ በበሽበጋምቤላ ክልል በኮሌራ ወረርሽኝ የሟቾች ቀጥር ከ30 መብለጡ ተገለጸ
በጋምቤላ ክልል በኑዌር ዞን በተከሠተው የኮሌራ ወረርሽኝ፣ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ30 በላይ ሰዎች መሞታቸውንና ከአንድ ሺሕ በላይ የሚደርሱ ደግሞ በበሽታው መታመማቸውን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ። የኑዌር ዞን ጤና መምሪያ ሓላፊ አቶ ጋትቤል ግርማ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ወረርሽኙ ቀድሞ የተከሠተባቸው ዋንታዎ እና አኮቦ ወረዳዎች፣ አኹንም ስርጭቱ ከፍተኛ እንደኾነ ጠቅሰው፣ መድኃኒትም በበቂ ኹኔታ አልቀረበም፤ ብለዋል። ከጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ ወደ ከፍተኛ አመራሮች ስልክ ብንደውልም ጥሪው ባለመነሣቱ ምክንያት ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም። Read more