newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር እንዳስታወቀው በኒዮርክ በሚገኘው የኮሎምብያ ዩንቨርስቲ ካምፓስና አካባቢው ባለው ፀረ ሴማዊ ትንኮየትረምፕ አስተዳደር ለኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ ሊሰጥ የነበረውን የ400 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ሰረዘ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር እንዳስታወቀው በኒዮርክ በሚገኘው የኮሎምብያ ዩንቨርስቲ ካምፓስና አካባቢው ባለው ፀረ ሴማዊ ትንኮሳ ምክንያት ለዩንቨርስቲው ሊሰጡ የነበሩ ወደ 400 ሚሊዮን ዶላር የሚገመቱ ዕርዳታዎችን እና ውሎችን መሰረዙን አስታውቋል፡፡ ውሳኔው ትላንት ይፋ የተደረገው የፍትህ፣ የትምህርት ፣ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት እንዲሁም የአጠቃላይ አገልግሎት አስተዳደር መምሪያዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው። የትራምፕ አስተዳደር የገንዘብ ድጎማዎች እና ውሎች በመቋረጡ ሊጎዱ የሚችሉትን ዘርፎች አልያም የፀረ ሴማዊ ትንኮሳ ማስረጃውን ለመግለጽ ፈቃደኛ አይደለም፡፡ ይሁንና ይህ ድጋፍ ለዩንቨርስቲው ቃል ከተገባለት ከ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ መካከል ተቀናሽ የሚሆን ነው ተብሏል፡፡ አብዛኛው የገንዘብ ድጋፍ ለጤና አጠባበቅና ሳይንሳዊ ምርምር የሚውል እንደሆነ ያስታወቀው የሮይተርስ ዘገባ አሃዞቹን ግን ማረጋገጥ አለመቻሉንም ገልጿል፡፡ ይፋ የተደረገው “የወዲያውኑ” ቅነሳዎች ህጋዊ ተግዳሮቶች ሊገጥሙት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡ የሲቪል መብት ተሟጋች ቡድኖች የኮንትራቱ መሰረዝ ተገቢውን ሂደት ያልተከተለና ጥበቃ ባላቸው መብቶች ላይ የተወሰደ ኢ-ህገመንግስታዊ ቅጣት ነው ሲሉ ተናግረዋል። ባለፈው አመት የእስራኤልና የጋዛ ጦርነት በተቀጣጠለበት ወቅት የኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ የፍልስጤም ደጋፊዎችና ጸረ እስራኤል የተማሪዎች ተቃውሞ በግንባር ቀደምትነት ሲካሄድበት የነበረ ነው፡፡ Read more