newsare.net
የየመን ሁቲ አማጽያን መሪ እስራኤል በአራት ቀናት ውስጥ በጋዛ ላይ የጣለችውን የእርዳታ እገዳ ካላነሳች ቡድኑ በእስራኤል ላይ የሚያደርገውን የባህር ሃይል ጥየየመን ሁቲዎች ለእስራኤል የጋዛን የእርዳታ እገዳ እንድታነሳ የአራት ቀናት ቀነ ገደብ ሰጡ
የየመን ሁቲ አማጽያን መሪ እስራኤል በአራት ቀናት ውስጥ በጋዛ ላይ የጣለችውን የእርዳታ እገዳ ካላነሳች ቡድኑ በእስራኤል ላይ የሚያደርገውን የባህር ሃይል ጥቃት እንደሚቀጥል ትላንት አስታውቋል፡፡ ይህም እ.ኤ.አ. በጥር ወር የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ እየቀነሰ የመጣው የሁቲዎች ጥቃት ሊባባስ እንደሚችል የሚጠቁም ነው ተብሏል፡፡ ኢራን አጋር የሆኑት የሁቲ አማጽያን እስራኤል በጋዛ በዩናይትድ ስቴትስ በሽብር የተፈረጀው ሃማስ ቡድን ላይ በከፈተችው ጦርነት ምክንያት ለፍልስጤማውያን አጋርነት ለማሳየት በሚል ከእአአ ህዳር 2023 ጀምሮ በመርከብ ላይ ያነጣጠሩ ከ100 በላይ ጥቃቶችን ፈጽሟል፡፡ መሪው አል-ሁቲ በኩል «ለአራት ቀናት ቀነ ገደብ እንሰጣለን፡ ይህም የጊዜ ገደብም ለጋዛ የተኩስ አቁም አሸማጋዮች ለጥረታቸው ሲባል ነው» ብሏል፡፡ እ.ኤ.አ መጋቢት 2 ጀምሮ እስራኤል የእርዳታ መኪኖችን ወደ ጋዛ እንዳይገቡ አግዳለች፡፡ ሃማስ እርዳታዎችን በመስረቅ ለፍልስጤማውያን እንዳይደርስ አድርጓል ስትልም ትከሳለች፡፡ Read more