newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት እንዳስታወቁት የፎክስ ኒውስ ፕሮግራም መሪ ላውራ ኢንግራሃምንና የጣቢያው ቢዝነስ ዘገባ አቅራቢ ማሪያፕሬዘዳንት ትራምፕ የቴሌቭዥን አቅራቢ የሆኑትን ላውራ ኢንግራሃምንና ማሪያ ባርቲሮሞን ለኬኔዲ ማዕከል ቦርድ አድርገው ሾሙ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት እንዳስታወቁት የፎክስ ኒውስ ፕሮግራም መሪ ላውራ ኢንግራሃምንና የጣቢያው ቢዝነስ ዘገባ አቅራቢ ማሪያ ባቲሮሞንን ለጆን ኤፍ ኬኔዲ የስነ ጥበባት ማዕከል ቦርድ ሹመዋል፡፡ ትራምፕ ስልጣን ከያዙ ከሳምንታት በኋላ የካቲት ወር ላይ የማዕከሉን ፕሬዝዳንት በማባረር የባለአደራ ቦርድ የተከኩ ሲሆን የድርጅቱን ሊቀመንበርም ሰይመዋል። ርምጃዎቹ የክብር ትርኢት የሚቀርቡበትና የብሄራዊ ሲምፎኒ ኦርኬስትራ እንዲሁም የዋሽንግተን ብሄራዊ ኦፔራ የሚቀርብበት የባህል ተቋም የሆነውን የኬኔዲ ማዕከል ትራምፕን መቆጣጠራቸውን ያሳያል ተብሏል፡፡ ትራምፕ የኢንግራሃም እና የባርቲሮሞ ሹመት ካስታወቁ በኋላ «ይህ ምርጫችንን ያጠናቅቃል» ሲሉ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡ ትራምፕ ባለፈው ወር የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ልዑክ የሆኑት ሪቻርድ ግሬኔል የማዕከሉ ጊዜያዊ ስራ አስፈፃሚ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመዋል፡፡ Read more