newsare.net
በአሜሪካ የጭነት ተሽከርካሪዎች ኩባንያ መስሎ በመቅረብ በቡና ላይ የሚፈጸም ዝርፊያ በመጨመር ላይ ነው። አሜሪካ በዓለም ከፍተኛ ቡና አስገቢ ሀገር ስትሆን፣የቡና ስርቆት በአሜሪካ
በአሜሪካ የጭነት ተሽከርካሪዎች ኩባንያ መስሎ በመቅረብ በቡና ላይ የሚፈጸም ዝርፊያ በመጨመር ላይ ነው። አሜሪካ በዓለም ከፍተኛ ቡና አስገቢ ሀገር ስትሆን፣ ባለፈው አንድ ዓመት ከዚህ በፊት ታይቶ በማያውቅ መጠን ዋጋው አሻቅቧል። ጉዳዩ ሂውስተን ውስጥ በተካሄደው የአሜሪካ ብሔራዊ የቡና ማኅበር ዓመታዊ ኮንፈረንስ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል። ቡና ሞቃታማ የአየር ንብረት ባላቸው ሀገራት የሚመረት በመኾኑ፣ በዓለም ቀዳሚ ቡና ጠጪ የሆነችው አሜሪካ ምርቱን መቶ በመቶ ከውጪ ለማስመጣት ተገዳለች፡፡ ምርቱ በአብዛኛው ከወደብ ወደ ቡና መቁያ ፋብሪካዎች የሚጓጓዘው በጭነት መኪና ነው። የዋጋውን መወደድ ያዩ ዘራፊዎች ታዲያ የጭነት ኩባንያ በመምሰል ቀርበው ቡናውን ጭነው ይሰወራሉ። ባለፈው አንድ ዓመት በደርዘን የሚቆጠሩ የጭነት መኪኖች ቡና ይዘው ተሰውረዋል። ቡና አምራች በሆኑ እንደ ብራዚል እና ቬትናም ባሉ ሀገራት ዝርፊያው የሚፈፀመው ገበሬዎች ምርቱን ሰብስበው ለጊዜው በሚያከማቹበት ሥፍራ ነው። ከአንድ ወር በፊት በብራዚል 230 ሺሕ ዶላር የሚያወጣ 500 ጆንያ ቡና በታጣቂዎች ተዘርፏል። በአሜሪካ ዝርፊያውን የሚፈጽሙት የትራንስፖርት ኩባንያ መስለው የሚቀርቡ ወሮበሎች ናቸው። አንድ የጭነት መኪና 20 ሺሕ ኪሎ ግራም የሚጠጋ ቡና ሲይዝ ይህም 180 ሺሕ ዶላር ይገመታል። ወሮበሎቹ የዘረፉትን፣ ቡና ለሚቆሉ አነስተኛ ኩባንያዎች በውድ ዋጋ ይሸጣሉ። አንዳንድ አስመጪዎች ታዲያ በጆንያው ላይ አቅጣጫ አመልካች መሣሪያ ለመግጠም ተገደዋል። Read more