newsare.net
በኢትዮጵያ ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ 7.3 ሚሊዮን ሰዎች በወባ መያዛቸውንና 1ሺሕ 157 በበሽታው መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በኢትዮጵያ 75 ከመቶ የሚበኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በወባ ተጠቅተዋል ተባለ
በኢትዮጵያ ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ 7.3 ሚሊዮን ሰዎች በወባ መያዛቸውንና 1ሺሕ 157 በበሽታው መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በኢትዮጵያ 75 ከመቶ የሚሆነው መሬት ለወባ ትንኝ ተጋላጭ በመሆኑ ለሃገሪቱ ከፍተኛ የጤና ተግዳሮት እንደደቀነም ድርጅቱ አስታውቋል። በእነዚህ አካባባዎች ከሚኖሩት ውስጥ 69 በመቶ የሚሆኑት በወባ የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ሲሆን፣ ከአምስት ዓመት በታች ሳሉ ከሚሞቱት ሕፃናት ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑት ሕይወታቸው የሚያልፈው በወባ ምክንያት መሆኑንም ዓለም አቀፉ የጤና ተቋም አስታውቋል። በተለይም ግጭት ባለባቸው ሥፍራዎች የጤና አገልግሎት ማዳረሡ አስቸጋሪ እንደሆነም የጤና ድርጅቱ ጠቁሟል። የሌሎች በሽታዎች መዛመትም ሁኔታውን ይበልጥ አስቸጋሪ እንዳደረገው ድርጅቱ አስታውቋል። Read more