newsare.net
ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ በአንድ ሌሊት የፈፀመች የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት እስከ ማለዳ ድረስ የዘለቀ እና ቢያንስ አንድ ሰው ማቁሰሉን የሩሲያ ሰዓታት በፈጀ የድሮን ጥቃት ኪቭን ዒላማ አደረገች
ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ በአንድ ሌሊት የፈፀመች የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት እስከ ማለዳ ድረስ የዘለቀ እና ቢያንስ አንድ ሰው ማቁሰሉን የከተማዋ ባለስልጣናት ዛሬ ቅዳሜ ተናገሩ። «የድሮኖቹ ስብርባሪዎች ስድስት የከተማ ወረዳዎች ላይ ሲወድቁ አንድ የፖሊስ መኮንን ቆስለዋል» ያሉት የከተማው ወታደራዊ አስተዳዳሪ ሰርሂ ፖፕኮ፣ በጥቃቱ የመኖሪያ ሕንፃዎች መውደማቸውንና እና የእሳት ቃጠሎ መነሳቱን ተናግረዋል ። የከተማዪቱ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ ቀደም ብለው በሰጡት መግለጫ ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውን ተናግረዋል። ፖፕኮ በማህበራዊ ሚዲያ መድረካቸው ላይ «ሌላ ምሽት፣ ሌላ የአየር ወረራ፣ ሌላ የማንቂያ ደወል፣ ሌላ ሰው አልባ ጥቃት፣ የሩስያ ፌዴሬሽን የታጠቁ ኃይሎች በቀድሞው እና በተለመደው ስልታቸው ኪቭ ላይ በድጋሚ ሌላ ጥቃት ሰንዝረዋል» ሲሉ ጽፈዋል፡፡ ፖፕኮ አክለውም “ኪቭ ላይ ያነጣጠሩ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በሙሉ ተመተው ወድቀዋል” ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ “ግን በአሁኑ ጊዜ ከከተማዋ ውጭ ባለው የአየር ክልል ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ድሮኖች ወደ ዋና ከተማዋ ሊዞሩ ይችላሉ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የሮይተርስ ዘጋቢዎች ከአምስት ሰዓታት በላይ በፈጀው የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ውስጥ በከተማው እና በአካባቢው ፍንዳታዎችን መስማታቸውን ዘግበዋል። የኪቭ ጦር ትላንት አርብ እንዳስታወቀው የሞስኮ ጦር በጥቅምት ወር ብቻ በዩክሬን በሚገኙ የሲቪል እና ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ “ከ2,000 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለጥቃት አሰማርቷል” ብሏል። ሩሲያ ጥቃቶችዋ በሲቪሎች ላይ ያነጣጠሩ ናቸው የሚለውን ስትቃወም “ የኃይል ማመንጫዎች የዩክሬን ወታደራዊ መሠረተ ልማት አካል ሲሆኑ ህጋዊ ዒላማዎች ናቸው” ብላለች ። Read more