newsare.net
በኢትዮጵያ የሰሜን ሸዋ ዞን ባለሥልጣናት አርብ ዕለት በተፈጸም ጥቃት አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን መገደላቸውን አስታውቀዋል። ባለሥልጣቱ የውጫሌ ወረዳ ዋየኦሮሞ ነጻነት ተዋጊዎች የሰሜን ሸዋ ዞን ባለሥልጣንን ገደሉ
በኢትዮጵያ የሰሜን ሸዋ ዞን ባለሥልጣናት አርብ ዕለት በተፈጸም ጥቃት አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን መገደላቸውን አስታውቀዋል። ባለሥልጣቱ የውጫሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ኮሩ ጉርሙ በታጠቁ ኃይሎች መገደላቸውን አስታውቀዋል። የግድያው ዜና በአካባቢው የብልጽግና ፓርቲ የፌስቡክ ገጽ ላይ ነው የሰፈረው። መግለጫው አቶ ንጉሴ “የተገደሉት” በካራ አካባቢ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ለመጎብኘት በተንቀሳቀሱበት ወቅት ነው በማለት አስፍሯል። ፓርቲው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት/ኦነግን ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርጓል። በጥቃቱ በመንግስት ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል በተፈጠረ ግጭት ሌሎች በርካታ ሰዎችመቁሰላቸውን እና መገደላቸውን የሚያመላክቱ ዘገባዎች አሉ። ‘አቶ ንጉሴ የህዝብ ፍላጎትን እና ጥቅምን ለማስከበር ቁርጠኝነት የነበራቸውና በህዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ በከፍተኛ ፍላጎት ህዝባቸውን የመሩ ናቸው’ በማለት የፓርቲው መግለጫ አስፍሯል። የአሜሪካ ድምጽ የውጫሌ ዞን የአካባቢ አመራሮች እና ከሰሜን ሸዋ አመራሮችን አግኝቶ ለማነጋገር ያደረገው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አማካሪ የሆኑት ጂሬኚ ጉደታ በውጫሌ ወረዳ የተደረገው ጥቃት በኦነግ መፈጸሙን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ በጥቃቱ እስካሁን ድረስ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ አላስታወቁም። Read more