newsare.net
ፈረንሳይ ውስጥ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎቹን ስለ ንግግር ነፃነት በሚያስተምርበት ወቅት የነቢዩ መሃመድን የካርቱን ምስል ካሳየ በኋላ በአንድ እስላማዊ ጽንፈኛከነብዩ መሃመድ የካርቱን ስዕል ጋር የተያያዘው የሽብር ጥቃት ወንጀል ጉዳይ መታየት ጀመረ
ፈረንሳይ ውስጥ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎቹን ስለ ንግግር ነፃነት በሚያስተምርበት ወቅት የነቢዩ መሃመድን የካርቱን ምስል ካሳየ በኋላ በአንድ እስላማዊ ጽንፈኛ በስለት ተቀልቶ በተገደለው መምሕር ሳሙኤ ፓቲ ላይ በተፈጸመው ወንጀል ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ ስምንት ሰዎች ጉዳይ መታየት ጀመረ። የዛሬውም የችሎት ውሎ በርካታ ፖሊሶች በተሰማሩበት ጥብቅ ፍተሻ እና ቁጥጥር መከናወኑ ተዘግቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ ከሚገኙት ተጠርጣሪዎች መካከል አምስቱ ከሰፊ የመስታወት ሳጥን ውስጥ እንዲቀመጡ ሲደረግ፤ የተቀሩት ሶስቱ እግሞ ተከሳሾቹ ከሚቀመጡበት ሥፍራ በቁጥጥር ስር ሆነው ቀርበዋል። ከተከሳሾቹ አራቱ የጂሃድ መልዕክት ሲያስተላልፉ በነበሩ የማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከነብሰ ገዳዩ ጋር ይወያዩ ነበር በሚል የሽብር ወንጀል ነው የተከሰሱት። ይሁንና መምምህሩን ለመግደል የተፈጸመውን ሴራ በተመለከተ የምናውቀው ነገር አልነበረም ሲሉ አስተባብለዋል። በሌላ በኩል ከፓሪስ ከተማ ወጣ ብሎ ከሚገኘው ትምሕርት ቤቱ አቅራቢያ የተፈጸመውን መምህር ፓቲ’ን አስደንጋጭ ግድያ ተከትሎም በርካታ ትምሕርት ቤቶች ለመታሰቢያው በስሙ ተሰይመዋል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ጥቅምት 16, 2020 መምሕሩን የገደለው ከሩስያዋ የቸቸን ክፍለ ግዛት የሆነው የ18 ዓመቱ ነብሰ ገዳይ በጊዜው በፖሊስ ጥይት ተደብድቦ መገደሉ ይታወሳል። Read more