newsare.net
ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የተካሄደው እ.አ.አ የ2024 ሀገር አቀፍ ምርጫ ውጤት በተለያዩ ግዛቶች መታወቅ ጀምሯል። እስካሁን ባለው ውጤት የሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንታዊ እትራምፕ እስካሁን 18 ግዛቶችን ሲያሸንፉ፣ ሃሪስ ዘጠኝ ግዛቶችን ማሸነፋቸውን አረጋግጠዋል
ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የተካሄደው እ.አ.አ የ2024 ሀገር አቀፍ ምርጫ ውጤት በተለያዩ ግዛቶች መታወቅ ጀምሯል። እስካሁን ባለው ውጤት የሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንታዊ እጩ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 18 ግዛቶች ውስጥ ማሸነፋቸውን ሲያረጋግጡ፣ የሪፐብሊካን እጩ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ዘጠኝ ግዛቶችን አሸንፈዋል። ትራምፕ ማሸነፋቸውን ያረጋገጡባቸው ግዛቶች በተለምዶ ለሪፐሊካን ፓርቲ ድምፃቸውን በመስጠት የሚታወቁት ኢንዲያና፣ ኬንታኪ፣ ዌስት ቨርጂኒያ፣ አላባማ፣ ኦክላሃማ፣ ሚሲሲፒ፣ ቴኔሲ፣ ፍሎሪዳ፣ ደቡብ ካሮላይና፣ አርካንሳ፣ ነብራስካ፣ ሰሜን ዳኮታ፣ ደቡብ ዳኮታ፣ ሉዚያና፣ ዋዮሚንግ፣ ኦሃዮ፣ ቴክሳስ እና ሚዙሪ ናቸው። ሃሪስ ማሸነፋቸውን ያረጋገጡባቸው በተለምዶ ዲሞክራትን በመምረጥ የሚታወቁት ቨርሞንት፣ ማሳቹሴትስ፣ ሜሪላንድ፣ ከነቲኬት፣ ሮድ አይላንድ፣ ኒው ጀርሲ፣ ዴላዌር፣ ኤሊኖስ እና ኒው ዮርክ ግዛቶች ናቸው። በዘንድሮ ምርጫ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚካሄድባቸው እና የምርጫውን ውጤት ለመለየት ወሳኝ ናቸው ተብለው የሚጠበቁት አሪዞና፣ ጆርጂያ፣ ሚቺጋን፣ ኔቫዳ፣ ሰሜን ካሮላይና፣ ፔንሴልቫኒያ እና ዊስኮንሰን ግዛቶች ውጤት እስካሁን አልታወቀም። Read more