newsare.net
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ፉክክር የተደረገባቸውን እንደ ፔንሴልቫኒያ እና ዊንስኮንሰን ያሉ ወሳኝ ግዛቶች ማሸነፋቸውዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ 47ኛ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ፉክክር የተደረገባቸውን እንደ ፔንሴልቫኒያ እና ዊንስኮንሰን ያሉ ወሳኝ ግዛቶች ማሸነፋቸውን ተከትሎ፣ ረቡዕ ጠዋት የአሜሪካ 47ኛ ፕሬዝዳንት ሆነው ማሸነፋቸውን አረጋግጠዋል። ትራምፕ፣ በግዛቶች ውስጥ በሚደረኩ ፉክክሮች ፈታኝ ፍልስሚያ በሚካሄድበት የዩናይትድ ስቴትስ የምርጫ ስርዓት ውስጥ የተፎካከሯቸውን ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ግልፅ በሆነ አብላጫ ድምፅ ማሸነፋቸው የታወቀው፣ ማክሰኞ እለት የድምፅ አሰጣጥ ሥርዓቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ነው። ትራምፕ ፈታኝ ፉክክር ይደረግባቸው ተብለው የተጠበቁትን ፔንሴልቫኒያ፣ ጆርጂያ እና ሰሜን ካሮላይና ግዛቶች ማሸነፋቸው ሥልጣኑን ለመረከብ ያስፈልጋቸው ከነበረው 270 የመራጮች ድምፅ ቢያንስ 267ቱን እንዲያገኙ ረድቷቸዋል። ዊስኮንሰን ግዛትም ረቡዕ ማለዳ ላይ ትራምፕ ማሸነፋቸውን አስታውቋል። በተጨማሪም ሪፐብሊካኖች 100 መቀመጫ ያለውን የሕግ መወሰኛ ምክርቤት መቆጣጠር የቻሉ ሲሆን፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤቱን ማን እንደሚያሸንፍ እስካሁን አልታወቀም። ትራምፕ ረቡዕ ማለዳ ላይ ፍሎሪዳ ውስጥ ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠው «ይህ ከዚህ በፊት ማንም አይቶት የማያውቀው እንቅስቃሴ ነው። እውነት ለመናገር እስከዛሬ ከተደረገው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሁሉ የላቀ ነው» ሲሉ ተናግረዋል። ትራምፕ በዚሁ ንግግራቸው «ድንበሮችን» እና ሌሎች ጉዳዮችንም እንደሚያስተካክሉ ቃል ገብተዋል። «ጠንካራ፣ አስተማማኝ እና የበለፀገች አሜሪካን» ለህዝቡ ለማቅረብ እንደሚሠሩም አመልክተዋል። የሃሪስ ዘመቻ ባለሥልጣን በበኩላቸው ዋሽንግተን ውስጥ ለተሰበሰቡት ደጋፊዎች ባደረጉት ንግግር ሃሪስ ንግግር የሚያደርጉት ረቡዕ ጠዋት መሆኑን ገልጸዋል። Read more