newsare.net
የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ (Federal Reserve) ለኢኮኖሚው ቁልፍ የሆነውን የወለድ ምጣኔ ትናንት ሐሙስ በሩብ ነጥብ ዝቅ እንዲል አድርጓል፡፡ ውሳኔው በአንድ ወቅት ከፍየአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ የወለድ መጠንን ዝቅ አደረገ
የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ (Federal Reserve) ለኢኮኖሚው ቁልፍ የሆነውን የወለድ ምጣኔ ትናንት ሐሙስ በሩብ ነጥብ ዝቅ እንዲል አድርጓል፡፡ ውሳኔው በአንድ ወቅት ከፍተኛ የዋጋ ንረት እያሽቆለቆለ መምጣቱን ተከትሎ አሜሪካውያንን ካስቆጣው የዋጋ ንረትና ግሽበት ጋራ የተያያዘ ሲሆን የቀድሞው ፕሬዝደንት ትረምፕን በዚህ ሳምንቱ ምርጫ እንዲያሸነፉ የረዳቸው መሆኑን ተመልክቷል፡፡ የወለድ ምጣኔው ቅነሳ በመስከረም ወር በግማሽ ነጥብ የቀነሰውን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ ማዕከላዊ ባንኩ ውሳኔው የሥራ ቅጥር ገበያውን ለመደገፍ፣ የዋጋ ንረንት ለመዋጋት እና አሁን ከባንኩ እቅድ 2 ከመቶ በላይ በመጠኑ ያለፈውን የግሽበቱን መጠን ለመቆጣጠር ያለመ ነው ብሏል፡፡ ባንኩ ለአራት አስርት ዓመታት እየከፋ የመጣውን የዋጋ ግሽበት ለመቋቋም የወለድ መጠኑን ከአንድ ዓመት በላይ ከፍ አድርጎ መቆየቱ ተገልጿል፡፡ ዓመታዊ የዋጋ ግሽበቱ እኤአ በ2022 አጋማሽ 9.1 ከመቶ ደርሶ የነበረ ሲሆን ባላፈው መስከረም በሶስት ዓመት ተኩል ውስጥ ዝቅተኛ ሆኖ ወደ ተመዘገበው 2.4 ከመቶ ዝቅ ብሏል፡፡ የሀሙሱ ውሳኔ በአራት አስርት ዓመታት ውስጥ 5.3 ከመቶ ደርሶ የነበረውን የወለድ መጠን ወደ ወደ 4.6 ከመቶ ዝቅ አድርጎታል፡፡ ማዕከላዊ ባንኩ የቅርብ ጊዜውን ስብሰባ ባጠናቀቀበት ወቅት በሰጠው መግለጫ “የሥራ አጠነት መጠኑ ከፍ ብሏል ቢሆንም መጠኑ ዝቅተኛ ነው” ብሏል፡፡ Read more