newsare.net
ሩሲያ ዩክሬን ውስጥ ዛሬ ዓርብ በኦዴሳ፣ ካርኪቭ እና ኪቭ ክልሎችን ኢላማ በማድረግ በድሮኖች፣ ሚሳይሎች እና ቦምቦች በፈጸመችው የአንድ ሌሊት ጥቃት አንድ ሰውሩሲያ ዩክሬንን በሚሳይል ድሮን እና ቦምቦች ደበደበች
ሩሲያ ዩክሬን ውስጥ ዛሬ ዓርብ በኦዴሳ፣ ካርኪቭ እና ኪቭ ክልሎችን ኢላማ በማድረግ በድሮኖች፣ ሚሳይሎች እና ቦምቦች በፈጸመችው የአንድ ሌሊት ጥቃት አንድ ሰው ሲሞት በትንሹ 25 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ጥቃቱ በመኖሪያ ሕንፃዎች እና መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ዛሬ ዓርብ በካርኪቭ የሩስያ ቦምብ ጥቃት የተመታ አንድ ባለ 12 ፎቅ የመኖሪያ ህንጻ የታችኞቹን ሶስት የፎቅ ክፍሎች አውድሟል፡፡ ኦዴሳ ውስጥ በሩሲያ ድሮኖች ከተመቱ የመኖሪያ ሕንፃዎች አንዱ በእሳት የተቀጣጠለ ሲሆን የ46 ዓመቱን ሰው ገድሎ ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎችን ያቆሰለ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ የዩክሬን ሀይሎች አራት ሚሳይሎችን እና በግምት 60 የሚጠጉ ድሮኖችን መትተው ማውረዳቸውን ገልጸው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሩሲያ ላይ የተጠናከረ የጋራ ርምጃ እንዲወስድ አሳስበዋል። ዜሌንስኪ ይህንን መልእክት ያስተላለፉት ቡዳፔስት ውስጥ በአውሮፓ የፖለቲካ ማህበረሰብ ስብሰባ ላይ ከአውሮፓ መሪዎች ጋር በተገናኙበት ወቅት ነው፡፡ የዩክሬንን መከላከያ ለማጠናከር የሚያስችሉ አዳዲስ ስምምነቶችን ከአውሮፓ መሪዎች ያገኙ መሆኑም ተመልክቷል፡፡ የዶናልድ ትረምፕ እና የቭላድሚር ፑቲን ወዳጅ ናቸው የተባሉት የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን በቅርቡ የአሜሪካ ምርጫ ባሸነፉት ትረምፕ አሜሪካውያን ለዩክሬን የሚሰጡት ድጋፍ ሊቆም እንደሚችል እና አውሮፓም በጦርነቱ ውስጥ የራሷን ተሳትፎ እንደገና እንድታጤነው ሀሳብ አቅርበዋል። የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ካሪን ዣን ፒየር እና የፔንታጎን ቃል አቀባይ ሳብሪና ሲንግን ጨምሮ የአሜሪካ ባለስልጣናት ፕሬዝዳንት ባይደን ስልጣን እስኪያዛውሩ ድረስ ለዩክሬን ዕርዳታ መስጠት እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡ ቀደም ሲል ለዩክሬን ደህንንነት ከተፈቀደው ውስጥ በግምት 2 ቢሊዮን ዶላር እና ተጨማሪ የ4 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያዎች አሁንም እንዳሉ መሆናቸውን የፔንታገን ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡ Read more