newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው በዩናይትድ ስቴትስ ምክርቤት የሚያገለግሉትን ኤሊዝ ስቴፋኒክ፣ የተባበሩትራምፕ ስቴፋኒክን የተባበሩት መንግስታት አምባሳደር እንዲሆኑ መረጡ
የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው በዩናይትድ ስቴትስ ምክርቤት የሚያገለግሉትን ኤሊዝ ስቴፋኒክ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አምባሳደር አድርገው መሾማቸውን አስታወቁ። ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ሰኞ ለሮይተርስ በላኩት መግለጫ «ኤሊዝ ስቴፋኒክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሆነው እንዲያገለግሉ በመሾሜ ክብር ይሰማኛል። ኤሊዝ በጣም ጠንካራ እና ብልህ የአሜሪካ ተፋላሚ ናቸው» ብለዋል። ኒው ዮርክን ወክለው በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የተመረጡት እና በምክርቤቱ የሪፐብሊካን ኮንፈረንስ ሊቀመንበር የሆኑት ስቴፋኒክ ጠንካራ የትራምፕ አጋር ሲሆኑ ሹመቱን አስመልክቶ አስተያየት እንዲሰጡ ወዲያው ማግኘት አልተቻለም። ትራምፕ ቅዳሜ እለት በሰጡት መግለጫ በሪፐብሊካን ፓርቲ ለፕሬዝዳንት እጩነት ተፎካካሪያቸው የነበሩትን ኒኪ ሄሊ እና የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው የነበሩትን ማይክ ፖምፔዮ በአዲሱ አስተዳደራቸው እንደማይካተቱ አስታውቀው ነበር። ሄሊ በቀደመው የትራምፕ አስተዳደር በመንግስታቱ ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል። ትራምፕ እ.አ.አ በጥር 20፣ 2025 ዓ.ም ቃለ መሃላ ፈፅመው ስልጣን ከመረከባቸው በፊት አስተዳደራቸው ውስጥ የሚያገለግሉ ሰዎችን ለመሾም እጩ ሆነው የቀረቡ ሰዎችን እያነጋገሩ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት ቅዳሜ እለት የገንዘብ ሚኒስቴር ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው ከታጩት፣ ታዋቂው ባለሀብት ስኮት ቤሰንት ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል። Read more