newsare.net
በቅርቡ በሞት የተለዩት የ94 ዓመቱ ካፒቴን መሐመድ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በደርግ የሥልጣን ዘመን ከውድቀት ከታደጉት ሰዎች አንዱና ጠንካራ አመራር እንደበቅርቡ ሕይወታቸው ያለፈው ካፒቴን መሐመድና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቆይታቸው በወዳጆቻቸው አንደበት
በቅርቡ በሞት የተለዩት የ94 ዓመቱ ካፒቴን መሐመድ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በደርግ የሥልጣን ዘመን ከውድቀት ከታደጉት ሰዎች አንዱና ጠንካራ አመራር እንደነበሩ በወቅቱ አብረዋቸው ያገለገሉ ባልደረባቸውና ወዳጃቸው ምስክርነታቸውን ሰጥተውላቸዋል። ሐረር ከተማ የተወለዱት ካፕቴን መሐመድ ፣ ከ1972 እስከ ከ1986 ዓ. የዋና ሥራ አስፈጻሚነት ኃላፊነታቸውን ጨምሮ ለ30 ዓመታት አየር መንገዱን አገልግለዋል። የአፍሪካ አቪዬሽን ማኅበር ፕሬዝዳንትም በመኾን ከሀገራቸው አልፈው ለአፍሪካ አየር መንገድ አስተዋጾ አድርገዋል። የአየር መንገዱ የቀድሞ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች፣ በወቅቱ የነበረው የካፒቴን መሐመድ አስተዋጾ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠው እንደኾነ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የአየር መንገድ ሥራ አስኪያጅና የካፒቴን መሐመድ አለቃ የነበሩት ካናዳ የሚገኙት ኮለኔል ሥምረት መድኽኔ፣ «ትውውቃችን የድሮ ነበር ሲሉ» ስለሟች ወዳጃቸውም በወቅቱ ስለነበረው የአየር መንገዱም ኹኔታ አጫውተውናል። የአየር መንገዱ የገበያና ኦፕሬሽን ዲሬክተር በመኾን ያገለገሉት የ90 ዓመቱ ካፕቴን አሰፋ አምባዬም ብዙ ዓመታትን ወደ ኋላ መልሰው፣ በወቅቱ ሊዘጋ ተቃርቦ የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከያሉበት ተሰብስበው እንዴት ሊታደጉት እንደቻሉ ተርከውልናል። «ከአየር መንገዱ ውጪ ኑሮም ሕይወትም አልነበረንም» ሲሉ የቀደመውን ጊዜያቸውን በትውስታ አጋርተውናል። የካፒቴን መሐመድ ልጅ አቶ ካሊድ መሀመድ ስለ አባታቸው፣ የአቪዬሽን አማካሪ አቶ ዮናታን መንክር ካሳም ስለቀድሞው የድርጅቱ መሪ የሚያውቁትን አካፍለውናል። Read more