newsare.net
ወደ 75 ሺሕ የሚጠጉ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ ወደ ኅብረተሰቡ መልሶ የማዋሐድና የማቋቋም ሥራ ነገ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሀድየቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሐድ ሥራ ነገ እንደሚጀምር ተገለጸ
ወደ 75 ሺሕ የሚጠጉ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ ወደ ኅብረተሰቡ መልሶ የማዋሐድና የማቋቋም ሥራ ነገ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን፣ ዛሬ አስታወቀ። በኢትዮጵያ መንግሥት በእና በህወሓት መካከል፣ ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ-ፕሪቶርያ ላይ የተደረገውን ተኩስ የማቆም የሰላም ስምምነት ተከትሎ፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ ወደ ኅብረተሰቡ መልሶ የማዋሐድና በማቋቋም መርሐ ግብር ከሁለት ዓመት መዘግየት በኋላ ነገ እንደሚጀምር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታውቋል። ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን፣ ዛሬ ኅዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ፣ ለዚህ ሥራ ሲባል በክልሉ የቀድሞ ተዋጊዎችን ተቀብሎ ለማሠልጠን የሚያስችሉ በመቐለ፣ በዕዳጋ ሐሙስና በዓድዋ ከተሞች ሦስት ማዕከላት መከፈታቸውን ተናግረዋል፡፡ ሒደቱም፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን ካሉበት የጦር እዝ በማላቀቅ ወደ ማዕከላት ማሰባሰብ፣ ማሰልጠን፣ ወደ ኅብረተሰቡ መቀላቀልና መልሶ ማቋቋምን እንደሚያካትት ኮሚሽነሩ ገልጸው፣ ይህንንም ነገ፣ ኅዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም መቐለ በሚገኘው የማሰልጠኛ ማዕከል እንደሚጀመር ጠቁመዋል። ኮሚሽነሩ፣ “በምዕራፍ አንድ የትግበራ መርሐ ግብር ፣ በዚህ ሳምንት ከትግራይ ክልል 75 ሺሕ የቀድሞ ተዋጊዎችን የሚያካትት ሥራ እንጀምራለን፡፡ በዚህ ዙር በአብዛኛው የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሴቶችና በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ትግበራውን እንጀምራለን፡፡” ብለዋል። የቀድሞ ተዋጊዎችን በአራት ወራት ለማቋቋም ከኢትዮጵያ መንግሥት አንድ ቢሊዮን ብር፣ ከዓለም አቀፍ ለጋሾች ደግሞ 60 ሚሊዮን ዶላር በጀት መገኘቱን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ ወደ መቐለ ማሰልጠኛ ማዕከል የሚገቡት የመጀመሪያዎቹ 320 የቀድሞ ተዋጊዎች፣ ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ እስከ ነገ ሙሉ ቀን የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተገኙበት፣ ትጥቅ የማስረከብ እንደሚያከናውኑም ኮሚሽነሩ አክለው ገልፀዋል። ስለጉዳዩ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርና ከጸጥታው ዘርፍ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡ /የዚህ ዘገባ ዝርዝር በምሽቱ የራዲዮ ፕሮግራም ይቀርባል/ Read more